ከሳምንት በፊት በቀድሞ ሚስቱ ዊትኒ ሃውስተን ድንገተኛ አሟሟት ላይ ለ”ቱዴይሾው” ቃለምልልስ የሰጠው ቦቢ ብራውን፤ ለ14 ዓመት በትዳር አብራው የኖረችው ዊትኒ የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛ ለመሆኗ ምክንያት በመሆኑ የተሰማውን ፀፀት ቢገልፅም ለደረሰባት ድንገተኛ ሞት ተጠያቂ መደረጉን ግን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በሙሉ ስሙ ሮበርት ባሪስፎርድ ተብሎ የሚጠራው ቦቢ ብራውን፤ ለ34 ዓመታት በቆየበት የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አራት አልበሞችን በመስራትከ8 ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ ለመሸጥ ችሏል - በመላው ዓለም፡፡