Tuesday, 20 March 2018 11:14

“የውብድንበር” ቅዳሜ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ የውብድንበር ነጋሽ “የውብድንበር” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው እውነተኛ ታሪክ ላይ ያተኮረ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ የበቃ ሲሆን የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው የቅርስና ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ እንደሚመረቅ ተገልጿል፡፡
ደራሲዋ በመፅሐፉ መግቢያ ላይ በሰፈረችው ማስታወሻ፤ “ያሳለፍኩት የህይወት ውጣ ውረድ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን የሚመለከትና ከታሪኩ የሚማሩት፣ አንዳንድ ይሆናሉ ብለው የማያስቧቸው ሁኔታዎች መሆናቸውን የሚያውቁበት፣ ምንም ዓይነት ሀሰት ያልተቀላቀለበት እውነተኛ ታሪክ በመፅሐፉ ቀርቧል…” ብላለች፡፡
በ427 ገፆች የተቀነበበው ይኼ ዳጎስ ያለ መፅሐፍ፤ ለአገር ውስጥ በ140፣ ለውጭ አገራት በ30 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡
 ‹ሽጉጤን ማን ሊወርስ ነው? ለጥቃቴ ማን ሊደርስ ነው?› ወዘተ በማለት የአባቴ ብስጭት ያስጨነቃት እናቴ ያረገዘችው 5ተኛ ልጅ ወንድ እንዲሆን የሁሉም ፀሎት ሲሆን ባለመሳካቱ ሁሉም ተደናግጠው፣ ወንድ ነው ብለው  ለአባቴ ይነግሯቸዋል፡፡ አባቴም ተደስተው ሽጉጥ ቢተኩሱም ቆይተው ሴት መሆኗን ሲያውቁ ተለያይተው፤ እናቴ ሌላ ባል አግብታ 5 ወንድ ልጆች ወለደች…” ይላል መፅሐፉ የሽፋን ጀርባ የቀረበው ቅንጭብ ታሪክ፡፡

Read 1542 times