በደራሲ ሙስተጃን ኢተም ተደርሶ በሳልቃን ፊልም ፕሮዳክሽን ዳይሬክት የተደረገው “ድንግሉ” የተሰኘ ፊልም ከነገ ወዲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በአምባሳደር ሲኒማ ይመረቃል፡፡ አስቂኝ የፍቅር ፊልም እንደሆነ የተነገረለት “ድንግሉ” የ1፡50 ደቂቃ ርዝመት ያለው ሲሆን አርቲስት ዓለማየሁ ታደሰ፣ አለምሰገድ ተስፋዬ፣ ሉሊት ገረመው፣ ሰላም ተስፋዬና ሌሎችም እንደተወኑበት ታውቋል፡፡ 1.5 ሚሊዮን ብር ወጥቶበታል የተባለውን ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት እንደፈጀ ተጠቁሟል፡፡
የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው በዚህ የፊልም ምርቃት ላይ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ የሳልቃን ፊልም ፕሮዳክሽን ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ዮሴፍ ካሳ ገልጿል፡፡ ሳልቃን ፊልም ፕሮዳክሽን ከዚህ ቀደም “አይገባንም” እና “አፄ ማንዴላ” የተሰኙ ፊልሞችን ለተመልካች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
Sunday, 25 February 2018 00:00
“ድንግሉ” ፊልም የፊታችን ሰኞ ይመረቃል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና