Saturday, 23 December 2017 10:57

“12ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የፊልም ፌስቲቫል” ሰኞ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


    “12ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የፊልም ፌስቲቫል”፤ከነገ በስቲያ ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት በብሔራዊ ቲያትር ይከፈታል፡፡ በዕለቱ አጫጭር ፊልሞች የሚታዩ ሲሆን በፌስቲቫሉ ላይ ተሳታፊ ፊልሞች ክሊፖች ይቀርባሉ፡፡ በዚህ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለዕይታ የተመረጠው ፊቸር ፊልም “Red leaves” የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን በእስራኤላዊ-ኢትዮጵያዊው የፊልም ዳይሬክተር የተሰራ ነው፡፡ ይሄ ትልቅ ሥነ ሥርዓት፤ የፊልም ባለሙያዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም አገር አቀፍና ዓለማቀፍ ሚዲያዎች በሚገኙበት ይከናወናል ተብሏል፡፡  
ሰኞ የሚከፈተው የፊልም ፌስቲቫሉ፤ እስከ ታህሳስ 23 ቀን 2010 ዓ.ም በመላው አዲስ አበባ በብሔራዊ ቲያትር፣ በቫማዳስ ሲኒማ፣ በሩሲያ የባህል ማዕከልና በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡  

Read 1579 times