የሚወዱህንና የሚያደንቁህን ንገረኝ፤ ያኔ ማንነትህን እነግርሃለሁ፡፡
በመደለልና በአድናቆት መካከል በአብዛኛው የጥላቻ ወንዝ ይፈሳል፡፡
የቤተሰብ ፍቅርና የጓደኞች አድናቆት ከሃብትና ጥቅም እጅግ የላቀ ነው፡፡
ከአድናቆት መፋታት የዝቅጠት ማረጋገጫ ነው፡፡
በህይወት ከ1ሺ ቃላት ይልቅ ተግባር ብዙ ይናገራል፡፡ በፍቅር ደግሞ ከምንም በላይ ዓይን ብዙ ይናገራል፡፡
በፍቅር መውደቅ ማለት ሰውየሽ ክንድሽ ላይ ተጋድሞ በህልምሽ ሲነቃ ነው፡፡
ከአሁን በኋላ ዳግም በፍቅር ባልወድቅ ግዴለኝም፡፡ ምክንያቱም ካንቺ ጋር በፍቅር የመኖር ዕድሉን አግኝቼአለሁና፡፡