Sunday, 07 May 2017 00:00

የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል "እውቅና ለማግኘት ተቸገርኩ" አለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

-    ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት ለመውሰድ ታቅዷል
 
   ከአንድ ዓመት በፊት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በ19 የሚዲያ ተቋማት የተመሰረተው የኢትዮጵያ ፕሬስ ካውንስል፤እስካሁን እውቅና የሚሰጠው አጥቶ መቸገሩ ተገለጸ፡፡
የካውንስሉ ሊቀመንበር አቶ አማረ አረጋዊ፤የሚዲያ ካውንስሉ አስፈላጊውን መስፈርቶች አሟልቶ የተቋቋመ ቢሆንም በህጋዊነት መዝግቦ፣እውቅና የሚሰጠው የመንግስት ተቋም አለመገኘቱን አስታውቀዋል፡፡ ካውንስሉ ሲቋቋም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤትን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ድጋፍ እንደቸሩ ያስታወሱት አቶ አማረ፤ከተቋቋመ በኋላ በሃገሪቱ ህግ መሠረት ተመዝግቦ ህጋዊ ስራ መጀመር ሲገባው የተለያዩ ምክንያቶች እየቀረቡ እስካሁን ዕውቅና ማግኘት አልቻለም ብለዋል፡፡ የመንግስት አካላት ጉዳዩን እንዲያጤኑትም ጠይቀዋል፡፡
የማህበራት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ወደሚመዘግበው ተቋም በተደጋጋሚ መመላለሳቸውን የተናገሩት የካውንስሉ ሊቀ መንበር፤‹‹እኛ የምንመዘግባችሁ በሚዲያ ተቋማት ዝርዝር አባልነት ሳይሆን በግለሰቦች ስም ሲሆን ነው›› የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውና ይህም አግባብ አለመሆኑን ለማስረዳት፣ የሆቴሎች ማህበር ሲመዘገብ በግለሰቦች አባልነት ዝርዝር ሳይሆን በተቋማት ስም መሆኑን  ቢጠቅሱም ተቀባይነት አለማግኘታቸውን ይገልጻሉ፡፡
ህገ መንግስቱ ያጎናጸፈውን በማህበር የመደራጀት መብት ለማስከበርም በቀጣይ ወደ ፍ/ቤት እንደሚያመሩ አቶ አማረ አስታውቀዋል፡፡

Read 1767 times