በወጣትና አንጋፋ ሴት የሥነ- ፅሁፍ ባለሙያዎች የተቋቋመው ‹‹ዜማ ብዕር›› የሴቶች የስነ ፅሁፍ ማህበር የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ዛሬ በራስ ሆቴል በድምቀት እንደሚያከብር የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሀኒሳ ሽኩር ገለፁ፡፡ በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ማህበሩ ያሳለፈው የ10 ዓመት ጉዞ ስኬትና ፈተና የሚወሳ ሲሆን የተለያዩ ግጥሞች፣ወጎችና ሌሎች የኪነ ጥበብ ፕሮግራሞች ለታዳሚ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ የስነ-ፅሁፍ ባለሙያዎችና የጥበብ ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ክብረ በዓሉን እንደሚታደሙ ታውቋል፡፡
Monday, 06 March 2017 00:00
‹‹ዜማ ብዕር›› 10ኛ አመቱን ዛሬ ያከብራል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና