Sunday, 18 December 2016 00:00

‹‹መቅረዝ›› ፊልም ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በዳንስ አሰልጣኙ ተመስገን መለሰ ተፅፎ፣ በዳግማዊ ፈይሳ የተዘጋጀው ‹‹መቅረዝ›› የዳንስና የባህል ፊልም የፊታችን ማክሰኞ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አምባሳደሮች፣ የዳንስ ባለሙያዎች፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል፡፡
1.5 ሚ ብር እንደወጣበት የተነገረለት ፊልሙ፤  በ‹‹ሬና›› ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራ ሲሆን  በ‹‹1,2,3 ስቱዲዮ›› ነው የቀረበው ‹‹መቅረዝ››  የ1፡45 ርዝማኔ ያለው ሲሆን ተሰርቶ ለመጠናቀቅ ስምንት አመት ፈጅቷል፡፡
በፊልሙ ላይ አስቴር አለማየሁ፣ መለሰ ወልዱ፣ ተመስገን መለሰ፣ ቃልኪዳን ታምሩና ከ1900 በላይ ተዋንያን ተካፍለውበታል፡፡ ፊልሙን ከ13 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት እንዳያዩት የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Read 608 times