“ጦቢያ ጃዝ” 65ኛውን የግጥም በጃዝ ምሽት የፊታችን ረቡዕ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በራስ ሆቴል አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
በዚህ ኪነ ጥበባዊ ፕሮግራም ላይ አንጋፋና ወጣት ገጣሚያን ‹‹ነፃ አውጭ›› በተባለው የሙዚቃ ባንድ ታጅበው ግጥሞቻቸውን ለታዳሚው እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ የጥበብ ምሽቱ አዘጋጅ እናት የማስታወቂያ ስራዎች ድርጅት ለአዲስ አድማስ እንደገለጸው፤ በመድረኩ ከግጥሞች በተጨማሪ ዲስኩርና መነባንብም ይቀርባሉ፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና