Monday, 05 December 2016 09:42

“የጥንቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ” ለሂስ ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በወርሃዊው የትራኮን የሂስ ጉባኤና የመፅሀፍት አውደ ርዕይ ላይ፣ በደራሲ መራሪስ አማን በላይ የተፃፈው “የጥንቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ” የተሰኘ መፅሀፍ ለሂስ ይቀርባል። በመፅሀፉ ላይ ሂስ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒርሲቲ የባህልና የስነ-ፅሁፍ አካዳሚ የስነ መለኮት መምህር ዶ/ር ስርግው ገላው እንደሆኑ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ በፍቅሩ ዳኛቸው ተናግረዋል፡፡
የዛሬ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ በሚካሄደውና “ክብሩ መፅሀፍት”፣ “ሊትማን ቡክስ” እና “እነሆ መፅሀፍት” በየወሩ መጨረሻ በጋራ በሚያዘጋጁት አውደ ርዕይ ላይ ለሂስ የተመረጠው መፅሀፍ፤ከአክሱም መመስረት በፊት እስከ ደርግ ውድቀት ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚዳስስ ነው ተብሏል፡፡ በአውደ ርዕዩ ላይ መጻህፍት ከ20-50 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎላቸው ለሽያጭ እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡

Read 4016 times