Monday, 03 October 2016 00:00

በሳምንቱ በኦሮሚያ 4 ወጣቶች መገደላቸውን ኦፌኮ አስታወቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(13 votes)

     ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የኦሮሚያ ወረዳዎች የ4 ሰዎች ህይወት በፀጥታ ኃይሎች ማለፉን ኦፌኮ ገለፀ፡፡
በነቀምት ላይ አንድ ወጣት መገደሉንና በምዕራብ መንዲ ወረዳ በመስቀል ደመራ ላይ የ15 ዓመት ታዳጊ መገደሉን የገለፀው ኦፌኮ፣ ነጆ በምትባል ከተማም አንድ ሰው ተገድሎ 5 ሰዎች በጥይት እንደቆሰሉ ጠቁሟል፡፡ በምዕራብ አርሲ አጄ፣ አንድ ሰው መሞቱን የተናገሩት የኦፌኮ ም/ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ፤ የማስፈራራትና ማዋከብ ዘመቻም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡
የኦህዴድ ሊቀ መንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ለማ መገርሳ፤ ከህዝብ ጎን እንደሚቆሙና ሰላም እንደሚፈጥሩ ቃል መግባታቸውን የጠቀሱት አቶ ሙላቱ፤ ይህ በተባለ ማግስትም በሰው ህይወትና አካል ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ካልቆሙ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡ ከክልሉ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

Read 2445 times