Sunday, 21 August 2016 00:00

“ሰባ ዘጠኝ (79)” ፊልም ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በተካበ ታዲዮስ ተፅፎ የተዘጋጀውና በስለሺ ጌታነህ ፕሮዲዪስ የተደረገው “ሰባ ዘጠኝ (79)” የተሰኘ ፊልም ከነገ ወዲያ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ይመረቃል፡፡ የሁለት ሰዓት ርዝመት ያለውና የፍቅር ድራማ ዘውግ የሆነው ፊልሙ፤ በ1979 ዓ.ም በነበረው ብሔራዊ ውትድርና እና የወጣቶች አፈሳ ላይ የሚያተኩር ሲሆን በወቅቱ ለአንድ ባለስልጣን የታጨች ልጃገረድ ነፃ ለመውጣት የምታደርገውን ትግል ያስቃኛል ተብሏል፡፡ ቀረፃው አራት ወራትን እንደፈጀ የተነገረለት ፊልሙ፤ከ1.7 ሚ. ብር በላይ እንደወጣበት ታውቋል፡፡ በፊልሙ ላይ ግሩም ኤርሚያስ፣ ሰላም ተስፋዬ፣ ናታይ ጌታቸውና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡ 

Read 1040 times