Saturday, 30 July 2016 12:12

“ትራኮን የመፅሀፍ ሂስና ጉባኤ” የዛሬ ሳምንት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በየወሩ መጨረሻ ባሉት ቅዳሜና እሁድ የሚካሄደው “ትራኮን የመፅሀፍ ሂስና ጉባኤ”፤የዛሬ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ በትራኮን ህንፃ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ “ሀሳብን በሀሳብ መፈተን” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የዚህ የመፅሀፍ ሂስና ጉባኤ ዋና አላማ፤ ሚዛናዊ የሆነ ሀሳብን ለመፍጠር፣ ፀሀፍትን ለማበረታታት፣ አንባቢያን ምን ማንበብ እንዳለባቸው ለመጠቆምና የመፅሀፍትን ፋይዳና ክብር ከፍ ለማድረግ እንደሆነ የ‹‹እነሆ›› መፅሀፍት መደብር ባለቤት አቶ በፍቅሩ ዳኛቸው ገልፀዋል፡፡
‹‹ክብሩ መፅሀፍት››፣ ‹‹ሊትማን ቡክስ›› እና ‹‹እነሆ መፅሀፍት›› በሚያዘጋጁት በዚህ ወርሃዊ የመፅሀፍት ሂስና ጉባኤ ላይ መፅሃፍት እየተመረጡ ለሂስ የሚቀርቡ ሲሆን በዚህኛው ዙር በአለቃ ተክለኢየሱስ ዋቅጅራ ተፅፎ አርትኦቱና ዝግጅቱ በዶ/ር ስርግው ገላው፤ በተሰራው “የኢትዮጵያ ታሪክ” የተሰኘ መፅሀፍ ላይ የታሪክ ምሁሩ አበባው አያሌው ሂስ ያቀርቡበታል ተብሏል፡፡ በሁለቱ ቀናት በጉባኤው ላይ የሚታደሙ ጎብኚዎች፣ የተለያዩ መፅሀፍትን ከ25 እስከ 50 በመቶ ቅናሽ ያገኛሉ የተባለ ሲሆን ሌሎች የኪነ ጥበብ ፕሮግራሞችም መዘጋጀታቸውን አቶ በፍቅሩ ገልፀዋል፡፡

Read 957 times