በጣይቱ የባህል ማዕከል በየዓመቱ የሚዘጋጀውና የአገሪቱን ሥነ-ፅሁፍ ማበረታታት ዋና አላማው አድርጐ የሚንቀሳቀሰው የኪነ- ጥበብ ምሽት የፊታችን አርብ ሀምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም “የጥበብ መዓዛ” በሚል ርእስ ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ጀምሮ በአክሱም ሆቴል ይካሄዳል፡፡በእለቱ ገጣሚ ሄኖክ ስጦታው፣ አዳም ሁሴን፣ በላይ በቀለ ወያ፣ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን፣ የምስራች ግርማ፣ ተክሉ ያለው፣ ሰይፉ ወርቁና ዳዊት ህሩይ ግጥሞቻቸውን ለታዳሚ የሚያቀርቡ ሲሆን በሙዚቀኛ ታምሩ ንጉሴ ይታጀባሉም ተብሏል፡፡ በተጨማሪም በመጋቤ ሐዲስና ሮዳስ ታደሰ “የህዋና የሥነ-ከዋክብት ጥናት በቀደምት ኢትዮጵያዊያን” የተሰኘ ጥናታዊ ገለፃ የሚካሄድ ሲሆን “ሁሉም በአገር ነው” የተሰኘ ዲስኩር በንግድ አመራር ባለሙያውና በአነቃቂ ንግግር አቅራቢው አቶ ሽመልስ ታደሰ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ “የጥበብ መዓዛ” የኪነ-ጥበብ ምሽት በተመሳሳይ ሳምንት የአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥም ይካሄዳል ተብሏል፡፡
Saturday, 02 July 2016 12:26
“የጥበብ መዓዛ” የኪነ- ጥበብ ምሽት ይካሄዳል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና