Monday, 30 May 2016 09:09

“ሔሮል” ፊልም በሀዋሳ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በደራሲ ዳንኤል ጌታቸው ተፅፎ፣ በኢዮብ አራጋው (ኢቢሪ) የተዘጋጀውና በሱፐር ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው “ሔሮል” የተሰኘው ፊልም ባለፈው ማክሰኞ ቦሌ በሚገኘው ሰራዊት ሲኒማ የተመረቀ ሲሆን ሐምሌ 28 ሀዋሳ በሚገኘው ሚሊኒየም አዳራሽ ይመረቃል ተብሏል፡፡የቤተሰብ ትራጀዲ ድራማ ዘውግ ያለው ፊልሙ፤ የ1፡32 ርዝማኔ ያለው ሲሆን 550 ሺህ ብር ወጪእንደተደረገበት ተገልጿል፡፡ ፍትህ በማግኘት ሩጫ ላይ የሚያተኩረው “ሔሮል”፤ ሙሉቀረፃው በሀዋሳ መካሄዱ ታውቋል፡፡ በፊልሙ ላይ ህፃን ኢዮብ ዳዊት፣ ሰለሞን ተካ፣ ፋንታስንታየሁ፣ አልማዝ አበበና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡

Read 715 times