Monday, 30 May 2016 09:08

“የቨርተር ሰቀቀኖች” ነገ ውይይት ይካሄድበታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  እናት የማስታወቂያ ድርጅት ከጐተ ኢንስቲትዩትና ከብሔራዊ ቤተ-መፃሕፍትና ቤተ - መዛግብት ጋር በመተባበር፣በጀርመናዊው ደራሲ በወልፍ ጋንግ ገተ በተፃፈውና በረዳት ፕሮፌሰር ተስፍዬ ገሰሰ “የቨርተር ሰቀቀኖች” በሚል ወደ አማርኛ በተመለሰው መጽሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት አቶ ዮናስ ታረቀኝ ሲሆኑ ማንኛውም በውይይቱ መሳተፍ የሚፈልግ ሰው መገኘት እንደሚችል ታውቋል፡፡

Read 665 times