Monday, 30 May 2016 09:07

“በኖት በህዳሪም” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

    ወደ እስራኤል አገር ለስራ ተጉዛ በመኖሪያ ፈቃድ እጦት ለእስር በተዳረገችው አብነት ከበደ የተፃፉ ወጐችና ግጥሞችን ያካተተው “በኖት በህደሪም” የተሰኘው መድበል ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ፀሐፊዋ በእስራኤል አገር የመኖሪያ ፈቃድ ሳትይዝ በመገኘቷ ከመንገድ ላይ ተይዛ ከርቸሌ የተወረወረች ሲሆን በሁለት ዓመታት የእስር ቆይታዋ ያሳለፈችውን መከራ በወቅቱ ከእነስሜቷ በሁለት ወጐችና በበርካታ ግጥሞች ከትባዋለች ተብሏል፡፡ መጽሐፉ ባለፈው ሳምንት የተመረቀ ሲሆን በ45 ብር እንደሚሸጥ ታውቋል፡፡

Read 739 times