Tuesday, 24 May 2016 08:42

ኢትዮጵያ የህፃናት መብትና ደህንነትን ፖሊሲ አላፀደቀችም

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(1 Vote)

 ረቂቁ ከ5 ዓመት በፊት ነው ለምክር ቤት የቀረበው
                                             
       ኢትዮጵያ የህፃናትን መብትና ደህንነት የሚያረጋግጥና የሚያስጠብቅ ፖሊሲ እስከ አሁን አላፀደቀችም፡፡ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያዚያ ወር 2003 ዓ.ም ያቀረበው የህፃናትን መብትና ደህንነትን የሚያስጠብቀው የመጨረሻ ረቂቅ ብሔራዊ የህፃናት ፖሊሲ እስከ አሁን ድረስ አለመፅደቁ ታውቋል፡፡ ሰሞኑን የጠቅላይ ኦዲተር መ/ቤት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት፤ የኦዲት ሪፖርቱ እስከተጠናቀቀበት እስከ ያዝነው ዓመት አጋማሽ ድረስ ፖሊሲው አለመፅደቁን ገልጿል፡፡  በጉዲፈቻ አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች አማካኝነት ወደ ውጪ አገር ስለሄዱ ህፃናት የላከው ድርጅት በወር፣ በስድስት ወር፣ በዓመትና ህፃኑ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ በሚቀጥሉት ተከታታይ ዓመታት በየዓመቱ ሪፖርቱን ለሚኒስቴር መ/ቤቱ መላክ የሚገባው ቢሆንም በዚህ መሰረት የማይፈፀም መሆኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

Read 1285 times