Saturday, 05 March 2016 10:48

“ሳዑዲ ካርጐ” አብረውት የሚሰሩ ደንበኞቹን ሸለመ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)

አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ስጋ በመላው ዓለም በማጓጓዝ የሚታወቀው “ሳዑዲ ካርጐ”፤ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አብረው የሚሰሩ ደንበኞቹን ሸለመ፡፡
በ2007 እ.ኤ.አ ካቤ ኩባንያን ጠቅላላ የሽያጭ ኤጀንቱ (GSA) አድርጐ መንገደኞችን በማጓጓዝ ሥራ የጀመረው “ሳዑዲ ካርጐ”፤ ከ2010 አንስቶ ቢሮውን በአዲስ አበባ በመክፈት በሳምንት ለሰባት ቀናት ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ አገራት ጠቅላላ የካርጐ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ አየር መንገዱ ሰሞኑን በሸራተን አዲስ ሆቴል ባካሄደው የአፍሪካ ክልል ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከናጀሪያ፤ ቻድና ደቡብ አፍሪካ ለመጡ ደንበኞቹ ዕውቅናና ሽልማት የሰጠ ሲሆን ደንበኞቹ ከሳዑዲ ከመጡ የኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስላለፈው የስራ ሁኔታና ወደፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተነጋግረዋል፡፡ ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በተካሄደው “አፍሪካ ኤየር ካርጐ” ኤግዚቢሽን ላይ ሳዑዲ “በመካከለኛው ምስራቅ በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኝ አየር መንገድ” በሚል መመረጡም ተገልጿል፡፡ ኩባንያው በመላው ዓለም ኔትወርኮች ያሉት ሲሆን በቀጣይ ከዚህ በበለጠ የሚበርባቸውን አገሮች በማብዛት አገልግሎቱን ለማስፋት ማቀዱንም የካርጐው ሴልስ ኤጀንት ማናጀር ተናግረዋል፡፡  

Read 2787 times