Saturday, 27 February 2016 11:15

በሻሸመኔ፣ በተወላጅነት ሰበብ የተከሰተው ችግር እንዲታረም ፓርቲዎቹ ጠየቁ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(11 votes)

    በሻሸመኔ አካባቢ “የኦሮሞ ተወላጅ”፣ “የወላይታ ተወላጅ” በሚል የተከሰተው ግጭትና ጥቃት  እንዳሳዘናቸው የገለፁ ሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች፤ በሰላምና በፍቅር አብሮ የመኖር ባህል መቀጠል እንዳለበት አሳሰቡ፡፡ የወላይታ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባርና የመላ ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ በሻሸመኔና በአጂ አካባቢ በተከሰተው ግጭት፤ በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ በሠላምና በፍቅር አብረው የዘለቁ ነዋሪዎች፤ አሁን የተከሰተውን ችግር በቀና ልቦና በመፍታት ሰላም እንዲሰፍን ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል፡፡ በክልሉ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም አጥጋቢ መፍትሔ አግኝቷል ማለት አይቻልም ያሉት ፓርቲዎቹ፤ ችግሮች ተመልሰው እንዳያገረሹ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ያሻል ብለዋል፡፡

Read 3632 times