Saturday, 20 February 2016 08:56

“The old and he Birth of New” ትላንት ተከፈተ

Written by  በናፍቆት ዮሴፍና በማሕሌት ኪዳነወልድ
Rate this item
(0 votes)

   የታዋቂው ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ የስዕል ስራዎች ለእይታ የሚቀርቡበት “The old and he birth of  New” የተሰኘ የስዕል ኤግዚቢሽን ትላንት ከቀኑ 11፡30 በዚሞዛይክ ሆቴል ተከፈተ፡፡ ለቀጣዮቹ 10 ቀናት ክፍት ሆኖ በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ሰዓሊው የተለያዩ እሳቤዎቹን ያንፀባረቀባቸው  በርካታ ስዕሎች ለዕይታ እንደሚቀርቡ ተጠቁሟል። ሰዓሊው ከዚህ ቀደም ሰባት የጋራና ሁለት የግል የስዕል ኤግዚቢሽኖችን በአገር ውስጥና ለአጭር ጊዜ ትምህርቱን በተከታተለበት ስፔይን ማቅረቡም ታውቋል፡፡ የስዕል ኤግዚቢሽኑን ያዘጋጀው ኢጋ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ነው ተብሏል፡፡ ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ፤ በ1997 ዓ.ም “ጨለማን ሰበራ”፣ በ1999 ዓ.ም ደግሞ “ለምን” የተሰኙ የግጥም መድበሎችን ለንባብ ማብቃቱም ይታወሳል፡፡

Read 1093 times