Saturday, 20 February 2016 08:53

“አትውለድ አትውደድ” ሰኞ ይመረቃል

Written by  በናፍቆት ዮሴፍና በማሕሌት ኪዳነወልድ
Rate this item
(0 votes)

    በግዕዝ ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራውና በናኦድ ጋሻው ተደርሶ የተዘጋጀው “አትውለድ አትውደድ” የተባለው ፊልም የፊታችን ሰኞ  ከቀኑ 10፡30 በብሔራዊ ቴያትር ይመረቃል፡፡ አርቲስት ዓለማየሁ ታደሰ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ደረጀ ኃይሌ እንዲሁም አንጋፋና ወጣት ሴት ተዋንያን የተሳተፉበት ይኸው ፊልም፤ሁሉንም አይነት ዘውጎች በውስጡ የያዘና በተለየ መንገድ የተሰራ እንደሆነ የግዕዝ ፊልም ፕሮዳክሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ አየለ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ለየት ያሉ ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡  

Read 1143 times