(ስለ ትምህረት)
- ትምህርት ሥልጣኔን የማስተላለፊያ መንገድ ነው፡፡
ዊል ዱራንት
- ልቡናን ሳያስተምሩ አዕምሮን ማስተማር ፈፅሞ ትምህርት አይባልም፡፡
አሪስቶትል
- ትምህርት ዓለምን ለመወለጥ ልትጠቀሙበት የምትችሉት እጅግ ሃያል መሳሪያ ነው፡፤
ኔልሰን ማንዴላ
- አስተማሪዎች በሩን ይከፍታሉ፤
የቻይናውያን አባባል
- የመማር ፍቅር አዳብሩ፡፡ ያኔ ፈፅሞ ማደግ አታቆሙም፡፡
አንቶኒ ጄ.ዲ'አንጄሎ
- አስተማሪዎች ፈተና መስጠት እስከቀጠሉ ድረስ ሁልጊዜም በትምሀርት ቤቶች ውስጥ ፀሎት መኖሩ አይቀርም፡፡
ምንጩ ያልታወቀ
- በመማር ታስተምራለችሁ፤ በማስተማር ትረዳላችሁ፡፡
የላቲኖች አባባል
- የራሳችን መንተድ ሳናበራ የሌሎችን መንገድ ለማብራት ችቦ ልንይዝ አንችልም፡፡
ቤን ስዊትላንድ
- ምንም ነገር ለማስተማር ብትፈልግ ቅልብጭ አድርገው፡፡
ሆራስ
- የትምህርት ዘጠኝ አስረኛው ማበረታታት ነው፡፡
አናቶሌ ፍራንስ
- የዘመናዊ የትምህርት ባለሙያ ተግባር ደኖችን ማጥፋት ሳይሆን በረሃን በመስኖ ማልማት ነው፡፡
ሲ.ኤስ.ሌዊስ
- እንዴት እንደሚታሰብ የሚያውቁ አስተማሪዎችን አይፈልጉም፡፡
ማሃትማ ጋንዲ
- የሚያደምጠው ካገኘ ሁሉም ሰው አስተማሪ ነው፡፡
ዶሪስ ሮበርትስ
- ምርጥ አስተማሪየችሁ ለመጨረሻ ጊዜ የሰራችሁ ስህተት ነው፡፡
ራልፍ ናዴር
Published in
ጥበብ