Monday, 11 January 2016 12:01

በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 140 ሰዎች መሞታቸውን ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታወቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(8 votes)

    ከማስተር ፕላኑ ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ 140 የሚደርሱ ዜጐች ህይወት መጥፋቱን ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታውቋል፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ትናንት ባወጣው ሪፖርት፤ የተቃዋሚ ፓርቲው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች አመራሮች መታሠራቸውን ተከትሎ ተቃውሞው ወደ አስጨናቂ ሁኔታ መቀየሩን ጠቅሷል።
መንግስት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን እንዲፈታና የፀጥታ ሃይሉ ከመጠን በላይ የሆነ ሃይል ከመጠቀም እንዲቆጠብ የጠየቀው ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ ዜጐች በሠላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ መፍቀድ እንዳለበትና ለጥያቄያቸውም ተገቢ ምላሽ ሊያገኙ እንሚገባ አመልክቷል፡፡
የክልሉ መንግስት በበኩሉ፤ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በጥንቃቄ ተጣርቶ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ያስታወቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽንና የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋማትም የችግሩን አጠቃላይ መንስኤና የደረሰውን ጉዳት እንደሚያጣሩ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡   

Read 3756 times