Saturday, 28 November 2015 14:17

“የማይታየውን በሚታይ” የስዕል ትርኢት ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   “የማይታየውን በሚታይ” የተሰኘው የሥዕል ትርኢት ትላንት ምሽት ሳርቤት ካናዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ጋለሪያ ቶሞካ ተከፈተ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የስነ-ጥበብና የዲዛይን ት/ቤት ከአንድ ዓመት በፊት የተመረቀው የወጣቱ ሰዓሊ የኪሩቤል አበበ ከ30 በላይ “ፊገራቲቭ” (አብስትራክት ያልሆኑ) ስራዎች የሚታዩበት ይህ የሥዕል ትርዒት፤ ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ለእይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ የጋለሪያ ቶሞካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ነብዩ ግርማ እንደገለጹት፤ትርኢቱ በተከፈተ በወሩ በሰዓሊው ስራዎችና በአሳሳል ፍልስፍናው  ላይ ሰዓሊያንና የሥዕል አፍቃሪያን በተገኙበት ውይይት ይካሄድበታል፡፡ 

Read 1004 times