Saturday, 14 November 2015 09:24

ኢ - መደበኛ በሆኑ የስራ መስኮች መሰማራት ውጤታማ ያደርጋል ተባለ

Written by  ማህሌት ኪ/ወልድ እና አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

       ከመደበኛ የትምህርት ስልጠና በተለየ እንደ ቧንቧ ሥራ ባሉ ኢ-መደበኛ የስራ መስኮች ላይ መሰማራት ውጤታማ ያደርጋል ሲል “ኮንሰርን ወርልድ ዋይድ ኢትዮጵያ” የተባለው ድርጅት ገለፀ፡፡ ከአዲስ ከተማ፣ ቂርቆስና ልደታ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ670 በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ቦንጋሴ እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ በዋናነት ገበያ ያላቸውንና ማህበራዊ ፍላጎት የሚንፀባረቅባቸውን የሥራ መስኮች በመለየትና ስልጠና በመስጠት ሰዎች ከድህነት እንዲወጡ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በቧንቧ ስራ፣ በጫማ ስራ፣ በብረታብረት ስራ፣ በጀሶ ስራ፣ በመኪና ቅብና መሰል ዘርፎች የተሰማሩት ሰልጣኞችም ውጤታማ ስራን በመስራት ለሌሎች አርአያ እየሆኑ ነው ተብሏል፡፡ ድርጅቱ ከአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ፣ ከአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በኢ-መደበኛ የሥራ መስኮች ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው ብለዋል - ምክትል ዳይሬክተሩ፡፡

Read 2166 times