Saturday, 07 November 2015 10:26

የደጃዝማች ክንፉ ኪዳኔ የህይወት ታሪክ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

      በደጃዝማች ክንፉ ኪዳኔ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነውና ከአንጥረኝነት እስከ ደጃዝማችነት ማዕረግ ያደረጉትን ጉዞ የሚያስቃኘው “ደጃዝማች ክንፉ ኪዳኔ፤ ከ1884-1964” የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡ በዘጠኝ ምዕራፎችና በተለያዩ ንዑስ ርእሶች የተከፋፈለው መፅሃፉ፤ ደጃዝማች ክንፉ በስራ ፈጠራቸው፣ በአንጥረኝነታቸውና በደጃዝማችነታቸው ዘመን ያሳለፏቸውን የህይወት ውጣ ውረዶች በዝርዝር ይተርካል ተብሏል፡፡ መፅሃፉ በልጃቸው ዮሐንስ ክንፉ ተዘጋጅቶ፣ በጋዜጠኛ ደረጀ ትእዛዙ አርታኢነት ለንባብ የበቃ ሲሆን በ122 ገፆች ተቀንብቦ በ50 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡

Read 3195 times