Saturday, 07 November 2015 10:01

ብሌስ ላቦራቶሪ፣ የውሃ ጥራትና የአፈር ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)

     በአገራችን ብቸኛው የግል ላቦራቶሪ ብሌስ አግሪ ፉድ ላቦራቶሪ ሰርቪስ፤ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ በተሰጠው ውክልና መሠረት የውሃ ጥራትና የአፈር ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ፣ የአይኤስኤ የላቦራቶሪ አክሪዴሽን ያገኘ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተቋም መሆኑን ጠቅሶ በአሁኑ ወቅት በርካታ የታሸጉ ውሃዎች ለገበያ እየቀረቡ ስለሆነ ላቦራቶሪው ከኢትዮጵያ ደረጀዎች ኤጀንሲ በተሰጠው ውክልና የውሃዎቹን የኬሚካል ይዘት፣ ከበሽታ አምጪ መርዛማ ኬሚካሎች ነፃ መሆናቸውን… (መርምሮ የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃን ካሟሉ የኤጀንሲውን አርማ እንዲጠቀሙ ፈቃድ መስጠቱ ከውሃ ጥራት ጉድለት የሚመጡትን በሽታዎች ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጿል፡፡
ብሌስ ላቦራቶሪ፣ በአፈር ምርመራው የአፈር ለምነትና እንደ ብረት፣ ሊድ፣ ፎስፈረስ፣… ያሉትን የሚኒራሎች መጠን መርምሮ ተገቢውን ግብአት እንዲጠቀሙ በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ተብሏል፡፡
የዘመኑ ቴክኖሎጂ ባፈራቸው የምርመራ መሳሪያዎች የተደራጀው ብሌስ አግሪ ፉድ ሰርቪስ ላቦራቶሪ በውሃ፣ በመጠጥና በእንስሳት መኖ ላይ የላቦራቶሪ ምርመራ  ከማድረጉም በላይ የአፍላቶክሲን (መርዛማ ኬሚካሎች) ምርመራ ለማድረግ አክሪዴሽን (እውቅና) ስላለው ወተትን ጨምሮ በጥራጥሬ፣ በቅመማ ቅመም፣ በቅባት እህሎች ከነተረፈ ምርታቸው፣… በመሳሰሉት ላይ የአፍላቶክሲን፣ ሌሎች ኬሚካሎችና ህዋስ ነክ ማይክሮባዮሎጂ ፍተሻዎች እያደረገ መሆኑን ላቦራቶሪው በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡


Read 2537 times