Saturday, 17 October 2015 11:29

የሰዓሊ ወርቁ ማሞ የክብርና ምስጋና ፕሮግራም ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     አቢሲኒያ የስነ-ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋም ከኢትዮጵያ ሰዓሊያንና ቀራፂያን ማህበር ጋር በመተባበር ለአንጋፋው ሰዓሊና መምህር ወርቁ ማሞ የክብር መግለጫ የምስጋና ምሽት ማዘጋጀቱን አቢሲኒያ የስነጥበብ ማሰልጠኛ አስታወቀ፡፡ከነገ በስቲያ ሰኞ ከ11፡30 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቲአትር በሚካሄደው ፕሮግራም፣ የሰዓሊው ስራዎች ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን የኮሜዲ ዝግጅትና ሌሎችም አዝናኝ ትርኢቶች መሰናዳታቸው ተ ጠቁሟል፡፡ ከ ዚህም በ ተጨማሪ የሰዓሊው የስዕል ስራዎች በኤግዚቢሽን መልክና በስላይድ ተደግፈው እንደሚቀርቡም ታውቋል፡፡ (ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ፕሮግራሙ ከነገ በስቲያ ሰኞ በሚል በዚያው ሳምንት እንደሚቀርብ ተደርጎ የተዘገበው በስህተት መሆኑን እየገለጽን፣አንባቢያንን ልባዊ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡   

Read 1238 times