Saturday, 17 October 2015 11:27

“የፊልም ድርሰት እንዴት ይፃፋል” ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)

    ዘፀአት በተባለ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ተፅፎ ለንባብ የበቃው “የፊልም ድርሰት እንዴት ይፃፋል” የተሰኘ መፅሀፍ ነገ ጠዋት ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር እንደሚመረቅ ደራሲውአስታወቀ፡፡ በ አገራችን የ ፊልም ስ ራና የ ፊልም ድርሰት አፃፃፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገው መፅሃፉ፤ወደዘርፉ አዲስ ለሚቀላቀሉ የፊልም ባለሙያዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡መፅሃፉ ለደራሲው የመጀመሪያው ቢሆንም በዘፈን ግጥምና በዜማ ድርሰት እንዲሁም በፊልምዳይሬክተርነት የመሥራት ልምድ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዓምና ለእይታ በበቃ ሳቅና ሙዚቃቪሲዲ ላይም በድርሰትና በዝግጅት ተሳትፏል፡ ፡ በ120 ገጾች ተቀንብቦ በ50 ብር ለገበያ የቀረበው
መፅሃፉ፤በነገው እለት ሲመረቅ የፊልም ባለሙያዎች፣ ፊልም አፍቃሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

Read 3755 times