Saturday, 10 October 2015 16:46

የኔታ ኪነጥበባትና ፕሮሞሽን 8ኛውን የግጥም በጃዝ ዝግጅት ያቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    የኔታ ኪነ-ጥበባትና ፕሮሞሽን ከ”ሪዲሞ ዘ ጀነሬሽን” ከተባለ አገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የፊታችን አርብ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በፓስፊክ ሆቴል አዳራሽ 8ኛውን የግጥም በጃዝ ዝግጅቱን ያቀርባል፡፡በእለቱ በዕውቅ ተጋባዥ ገጣሚያን የግጥም ሥራዎች በጃዝ ታጅበው የሚቀርቡ  እንደሆነ የኔታ ኪነ-ጥበባት አስታውቋል፡፡ ከግጥም በተጨማሪም ዲስኩር፣ አጭር ተውኔት፣ ምርጥ ደብዳቤና ወግ ለታዳሚው እንደሚቀርቡ የተገለፀ ሲሆን ታዋቂው ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ለታዳሚያን ሥነፅሁፋዊ ስራውን እንደሚያቀርብ አዘጋጁ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡  

Read 1346 times