Saturday, 10 October 2015 16:45

ለሰዓሊ ወርቁ ማሞ የክብርና የምስጋና ፕሮግራም ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

አቢሲኒያ የስነ - ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋም ከኢትዮጵያ ሰዓሊያንና ቀራፂያን ማህበር ጋር በመተባበር ለአንጋፋው ሰዓሊና መምህር ወርቁ ማሞ የክብር መግለጫ የምስጋና ምሽት ያዘጋጀ ሲሆን፤ ከነገ በስቲያ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ፕሮግራሙ ይካሄዳል፡፡
በዚህ የክብርና የምስጋና መግለጫ ፕሮግራም ላይ መምህር ወርቁን የሚዘክሩና ለእርሳቸው ክብር የተሰናዱ ዝግጅቶች ለታዳሚዎች እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1360 times