Saturday, 10 October 2015 16:44

የሲድኒ ሰልማን “The Ultimate Challenge” ኮንሰርት ተካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ትላንት ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ “The Ultimate Challenge” የተሰኘው የሲድኒ ሳልመን ኮንሰርት በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ ተካሄደ፡፡ ታዋቂው የሬጌ ሙዚቃ ተጫዋች ሳልማን ኮንሰርቱን ያቀረበው “ኢምፔሪያል ማጀስቲክ” በተባለው የራሱ ባንድ ታጅቦ ነው፡፡ የሙዚቃ ድግሱ ያለ ክፍያ በነፃ የቀረበ ሲሆን በቅርቡ የሚለቀቀውን “The Ultimate Challenge” የተሰኘ ሙሉ አልበሙን ለማስተዋወቅና ቀድሞ ቪዲዮው የተለቀቀውን ነጠላ ዜማ (“The Ultimate Challenge”) ለማስመረቅ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ድምፃዊው ገልጿል፡፡የአልበሙ መጠሪያ የሆነው ይኸው ሙዚቃ፤ እ.ኤ.አ በ1963 ዓ.ም ንጉስ ኃይለስላሴ በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ስለ ዘር፣ ቀለምና አድልዎ ያደረገሩትን ንግግር መነሻ አድርጐ የተሰራ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 891 times