Friday, 11 September 2015 10:01

“በቀጣይ አመት ብሩህ ተስፋ አለን” አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ (የሙለር ሪል እስቴት ባለቤት)

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

      ያለፈው የስራ ዘመናችን መጠነኛ ነበር፡፡ የስራ እንቅስቃሴዎቹ ደህና ናቸው፡፡ ያለፉት አመታት ላይ አጥልቶ የነበረው የስራዎች መጓተት በዚህኛውም ላይ አጥልቶ ነበረ፡፡ በዚህ ምክንያት እንቅስቃሴያችን መጠነኛ ነበር፡፡
በቀጣይ አመት ግን ብሩህ ተስፋ እናያለን፡፡ በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው፤የመልካም አስተዳደር ችግር ተቀርፎ፣ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የማጠናከሪያ ድጋፍ እየተደረገ ይሄዳል የሚል እምነት አለን፡፡ የሪል እስቴት ግዢና ሽያጭ ህግም ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እሱም በሪል እስቴት ላይ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ይኖረው ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ መጪው ጊዜ ብሩህ ነው ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብም ሰላም፣ ጤናና፣ ፍቅር ይብዛለት!

Read 1702 times