Monday, 05 January 2015 08:32

“የአዕምሮ ጉዳይ 2” እና “የአዕምሮ ጉዳይ 3” ለንባብ በቁ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    በኢ/ር ወንድሙ ነጋሽ በአዕምሮ ጤና ላይ የማህበረሰቡን አመለካከት ለመለወጥ ይረዳሉ ተብለው የተዘጋጁት “የአዕምሮ ጉዳይ 2” እና “የአዕምሮ ጉዳይ 3” መፅሀፎች ሰሞኑን ለንባብ በቁ፡፡ “የአዕምሮ ጉዳይ 2” አስተሳሰብን የመግራት ህክምና (cognitive behavioral therapy) ላይ የሚያተኩር ሲሆን ራስን ለመቀየር አስተሳሰብን የመቀየር አስፈላጊነት ላይ ያነጣጥራል፡፡ በ128 ገፅ የተመጠነው መፅሀፉ፤ ለአገር ውስጥ በ35 ብር፣ ለውጭ በ15 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ “የአዕምሮ ጉዳይ” 3 መፅሀፍ ደግሞ በተለይ በአመለካከት መዛባት፣ በድብርት፣ በውጥረት፣ በእንቅልፍ ማጣት፣ በስብዕና መዋዠቅ፣ ባልተገባ ስጋት፣ በመዘንጋት፣ በሃዘን፣ በጥርጣሬና በሌሎች ለአዕምሮ ህመም በሚያጋልጡ ችግሮችና በመፍትሄዎቻቸው ዙሪያ የሚያተኩር ነው ተብሏል፡፡ ሲሆን በ15 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በተመሳሳይ ዋጋ ነው ለገበያ የቀረበው፡፡ ነዋሪነታቸውን በእንግሊዝ ያደረጉት ኢ/ር ወንድሙ ነጋሽ፤ ከዚህ ቀደም በአዕምሮ ጤና ላይ የሚያጠነጥኑ “ፍቅር ምንድን ነው”፣ “የአዕምሮ አስተዳደር ሞዴል” እና “የአዕምሮ ጓዳ 1” የተሰኙ መፅሀፎችን ማሳተማቸው ይታወሳል፡፡

Read 1577 times