Monday, 05 January 2015 08:31

ማሳቅ፣ ማሳዘን፣ማሸበር” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

    በጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም የተፃፈው “ማሳቅ፣ ማሳዘን፣ ማሸበር” የተሰኘ መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ የመፅሀፉ ይዘት ፖለቲካዊ ቧልት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ 20 ያህል ታሪኮችን የያዘውና  በ176 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ49 ብር ይሸጣል፡፡ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም ከዚህ ቀደም “አስራ ሰባት መርፌና ሃያ ምናምን ቁምጣ” የተሰኘ የወግ መፅሀፍ ለአንባብያን ማድረሱ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት በስደት ላይ የሚገኘው ሃብታሙ ስዩም፤ በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ የሸገር ሼልፍ ፕሮግራም አዘጋጅ፣ በኋላም የ“አዲስ ጉዳይ” መፅሄት አምደኛ በመሆን የሰራ ሲሆን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን “የብራና ልጆች” የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢም ነበር፡፡

Read 2438 times