Saturday, 02 August 2014 12:07

የፍቅር ጥግ

Written by 
Rate this item
(9 votes)

ፍቅር እንደ ቫይረስ ነው፤ ማንም ሰው ላይ በማንኛውም ሰዓት ሊከሰት ይችላል፡፡
ማያ አንጄሎ
ወንዶችን ካልወደድሻቸው እላይሽ ላይ ይሰፍሩብሻል፤ የወደድሻቸው ስትመስያቸው ግን ከመቅፅበት ፊታቸውን ያዞሩብሻል፡፡
ቢዮንሴ ኖውሌስ
ፈፅሞ አፍቅራ የማታውቅ ሴት ጨርሶ ኖረች ልትባል አትችልም፡፡
ጆን ጌይ
(እንግሊዛዊ ገጣሚና ፀሃፌ ተውኔት)
ለፍቅር መድሃኒቱ የበለጠ ማፍቀር ብቻ ነው፡፡
ሔነሪ ብሮሜል
ምንጊዜም በፍቅር ውስጥ ጥቂት እብደት አይጠፋም፤ በእብደት ውስጥ ግን ሁልጊዜም ጥቂት ምክንያት ይኖራል፡፡
ዩሪፒደስ
የምናፈቅረው እንከን የለሽ ሰው ፈልገን አይደለም፡፡ እንከን ያለበትን ሰው እንከን አልባ አድርጎ መመልከትን  በመለማመድ ነው፡፡
ሳም ኪን
(To Love and Be Loved)
ማፍቀር ከረዥም ህንፃ ላይ እንደ መዝለል ነው። አዕምሮህ የሚያዋጣ ሃሳብ እንዳልሆነ ይነግርሃል፤ ልብህ ግን መብረር እንደምትችል ሹክ ይልሃል፡፡
ማፍቀርና መፈቀር ፀሃይን ከሁለቱም ወገን ማግኘት ነው፡፡
ዴቪድ ፎስተር

Read 5581 times