Saturday, 02 August 2014 11:58

“አይንሽ አመሌ ነው” እና “እንዳወዳደቄ”ለአድማጭ ቀረቡ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በወጣት ድምፃዊ ሚሊዮን አበባ (ሚላ) የተቀነቀኑት “አይንሽ አመሌ ነው” እና “እንዳወዳደቄ” የተሰኙ ሁለት ነጠላ ዜማዎች ለአድማጭ ጆሮ መብቃታቸውን ድምፃዊው ገልጿል፡፡ ከተለያዩ ታዋቂ ድምፃዊያን ጋር በተለያዩ የምሽት ክበቦች ሲሰራ የቆየው ድምፃዊ ሚሊዮን፤ ሙሉ አልበም ለማውጣት ሲጥር ቢቆይም ሳይሳካለት መቆየቱንና እነዚህን ሁለት ነጠላ ዜማዎች  ለአድማጭ ጆሮ ማብቃቱን ተናግሯል፡፡ “አይንሽ አመሌ ነው” የተሰኘው ነጠላ ዜማ፣ ግጥሙ በዮናታን አሰፋ የተሰራ ሲሆን ዜማው በተስፋዬ ሽታ መሰራቱም ታውቋል “እንዳወዳደቄ” የተሰኘው ዜማና ግጥም ደግሞ በዮናታን አሰፋ ተሰርቶ ሁለቱም ዘፈኖች በአዲስ ይማም መቀናበራቸውን ድምፃዊው ገልፆ፤ እነዚህን ዘፈኖች ለአድማጭ ጆሮ ለማድረስ ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገለት አትሌት ወርቁ ቢቂላ ምስጋና አቅርቧል፡፡

Read 2004 times