Saturday, 02 August 2014 11:56

“አደሞን ለመስፍን” የኪነ-ጥበብ ፕሮግራም ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በቅርቡ በሞት ለተለየው ታላቁ የወግ ጸሐፊ፤ ደራሲና ሃያሲ መስፍን ወ/ማርያም ልጆች ገቢ ማሰባሰቢያ የሚውል “አደሞን ለመስፍን” የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ነሐሴ 3 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ በብሄራዊ ሙዚየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት በዶ/ር ሙሴ ያእቆብ ተፅፎ ለህትመት የበቃውን “አደሞ” የተሰኘ መፅሀፍ ለሽያጭ በማቅረብ ከሽያጩ የሚገኘውን ሙሉ ገቢ ለአቅመ አዳም ያልደረሱትን የመስፍን ሃ/ማርያም ልጆች ለመደገፍ እንደሚውል የ“አደምን ለመስፍን” የኪነ ጥበብ አዘጋጅ ኮሚቴ ዶ/ር ሙሴ ያዕቆብ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ታላቁ የወግ ፀሐፊ በመጨረሻ የእስትንፋሱ ማብቂያ ሰዓታት ላይ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሁለት ልጆቹ እንዳይረሱ በመወትወት በ“ቃል ዕዳ” ጓደኞቹን ተማፅኖ ህይወቱ ማለፉን ያስታወሱት የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ ይህንን አደራ ለመወጣት ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ መስፍንን የሚወድና የሚያደንቅ ማንኛውም ሰው በኪነ-ጥበብ ዝግጅቱ ላይ በመገኘትና መፅሀፉን በመግዛት ግዴታውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

Read 1067 times