Saturday, 14 December 2013 13:21

“የሴት ልጅ” ረጅም ልቦለድ ነገ በአዳማ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(1 Vote)

በመምህር ደሴ ጌታሆን የተፃፈውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው “የሴት ልጅ” ልቦለድ መፅሃፍ ነገ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጀምሮ አዳማ በሚገኘው አዳማ ራስ ሆቴል ይመረቃል፡፡
492 ገፆች ያሉት መፅሃፍ፤ በ80 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው መምህር ደሴ ጌታሁን ከ30 ዓመት በላይ በመምህርነት ከማገልገላቸውም በላይ በእንስሳት ሀኪምነትም እንደሰሩ ተጠቁሟል፡፡ የአዳማ ነዋሪ የሆኑት መምህር ደሴ፤ “ሰው” የተሰኘ የግጥም መድብል ለማሳተምም በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በመፅሃፉ ምርቃት ላይ የኪነጥበብ ባለሙያው አርቲስት ጌትነት እንየውን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችና ጋዜጠኞች ይገኛሉም ተብሏል።

Read 3064 times