Saturday, 14 December 2013 13:14

70 ወጣት ሰዓሊያን ተሳትፈውበታል የስዕል ባዛር በጣይቱ ሆቴል ተከፈተ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

የ 70 ወጣት ሰዓሊያንን ስራ ለተመልካች ይፋ ያደረገ የስዕል ኤግዚቢሽን ትላንት በ8 ሰዓት በጣይቱ ሆቴል ተከፈተ፡፡ “አርት ፌር” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው አውደርዕይ፤ 500 የሚጠጉ ስዕሎችን ያካተተ ሲሆን  እስከ ነገ ማታ ድረስ ለተመልካች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቀደም ሲል እንዲህ ዓይነት የስዕል ባዛር በተለያዩ ስፍራዎች የተዘጋጀ ቢሆንም በጣይቱ ሆቴል  ሲስተናገድ ግን የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

Read 1034 times