የእህል ወፍጮ ሚዛን የሰረቀው የ4 ዓመት እስር ተበይኖበታል
ከሌሊቱ 9 ሠአት ላይ በካዛንቺስ፣ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ ታጥበው የተሰጡ 3 ጅንስ ሱሪዎችን ደራርቦ በመልበስ
ሠርቆ ሲወጣ የተያዘው ተከሣሽ ሀቢብ አብደላ ኑሪ፤ በፈፀመው ወንጀል በ2 አመት እስራት እንዲቀጣ የፌደራሉ ከፍተኛ
ፍ/ቤት ሠሞኑን ብያኔ ሰጥቷል፡፡
ተከሣሹ የዛሬ ሦስት ሳምንት ህዳር 2 ሌሊት በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ጥይት ፋብሪካ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ
መኖሪያ ግቢ እያንዳንዳቸው 600 ብር የሚያወጡ ሶስት ጅንስ ሱሪዎችን የራሱ አስመስሎ ደራርቦ በመልበስ ሰርቆ
ሲወጣ መያዙ ተገልጿል፡፡ ፍ/ቤቱም ሠሞኑን “የተከሣሹ ድርጊት ሌሎችንም ያስተምራል” በሚል በ2 አመት እስራት
እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
በሌላ በኩል በልደታ ክ/ከተማ የግለሠቦችን መኖሪያ ግቢ ሠብሮ በመግባት 5ሺህ ብር የሚገመት የእህል ወፍጮ ሚዛን
የሠረቀውና በሊስትሮነት የሚተዳደረው ወጣት ሠለሞን ፀጋዬ ላይ የ4 አመት እስራት በይኖበታል፡፡
Saturday, 30 November 2013 10:39
ሶስት ሱሪዎችን ደራርቦ በመልበስ ሠርቆ ሲወጣ የተያዘው ተፈረደበት
Written by አለማየሁ አንበሴ
Published in
ዜና