* ውሸት ፍጥነት አለው፤ እውነት ደግሞ ፅናት፡፡
ኤዴጋር ጄ. ሞህን
* እጅግ አደገኛ ውሸት የሚሆኑት በጥቂቱ የተዛቡ እውነቶች ናቸው፡፡
ጆርጅ ክሪስቶፍ ሊችተንበርግ
* ግማሽ እውነት ማለት ሙሉ ውሸት ነው፡፡
የአይሁዳውያን አባባል
* ለአንተ ብሎ የዋሸ፣ በአንተ ላይም መዋሸቱ አይቀርም፡፡
የቦስኒያዎች አባባል
* ማንንም ስለማልፈራ ጨርሶ አልዋሽም፡፡
የምትዋሸው የምትፈራ ሲሆን ብቻ ነው ፡፡
ጆን ጎቲ
* ሁሌም ጨካኝ ሳይሆኑ ሃቀኛ የመሆኛ
መንገድ አለ፡፡
አርተር ዶብሪን
* እንደማንኛውም ውድ እቃዎች ሁሉ
እውነትም ብዙ ጊዜ ይጭበረበራል፡፡
ጄምስ ካርዲናል ጊቦንስ
* እውነትን ማበላሸት ከፈለግህ ለጥጠው፡፡
ያልታወቀ ደራሲ
* ውሸት ስትናገር የአንድን ሰው እውነት
የመስማት መብት እየሰረቅህ ነው፡፡
ካሊድ ሆስኒ
* ብዋሽ ግዴለኝም፤ ትክክል አለመሆን ግን ያስጠላኛል፡፡
ሳሙኤል በትለር
* ሃቀኝነት የጥበብ መፅሐፍ የመጀመርያው
ምዕራፍ ነው፡፡
ቶማስ ጄፈርሰን
* ውሸት ከመናገር የበለጠ የሚከፋው ቀሪ ህይወትን ለውሸት ታማኝ ሆኖ መኖር ነው፡፡
ሮበርት ብራውልት
Published in
የግጥም ጥግ