ወጣት ገጣሚያንና የሙዚቃ ባለሙያዎች የተቀናጁበት ወርሃዊ የኪነጥበብ ዝግጅት በመጪው ረቡዕ ምሽት 12፡30 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይቀርባል፡፡ ገጣሚና ተዋናይ ሜሮን ጌትነት መድረክ በምትመራበት ዝግጅት ረዳት ፕሮፌሰር ኃይማኖት አለሙ ከ“ቴዎድሮስ” ትያትር ቅንጭብ የሚያቀርብ ሲሆን፣ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ መነባንብ፣ አባባው መላኩ፣ በረከት በላይነህ፣ ቸርነት ወልደገብርኤል፣ ምልዕቲ ኪሮስና ሌሎችም የግጥም ሥራዎቻቸውን ከመለከት ባንድ የጃዝ ሙዚቃዎች ጋር በማጣመር ያቀርባሉ፡፡ የመግቢያ ዋጋውም 50 ብር እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡