ሥለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው የፊልሙ ፕሮዲዩሰር አቶ ዮናስ ጌታቸው፤ በሥህተት የተበላሸ ሲዲ ወደ ሲኒማ አምባሳደር መላኩንና በ10 ሰዓት እና በ12 ሰዓት በነበሩ ዝግጅቶች መታረሙንተናግረው፣ በሥህተቱ የተንገላቱ ተመልካቾችን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት ፊልሙ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ በድጋሚ እንደሚመረቅ ገልፀዋል፡፡
ባለፈው እሁድ ከቀኑ 8 ሰዓት “ደርቢ” የአማርኛ ፊልምን ሊመለከቱ የገቡ ፊልም አፍቃሪዎች በፊልሙ የድምፅ ጥራት መጓደል የተሰማቸውን ቅሬታ ገለፁ፡፡ በአምባሳደር ሲኒማ ገንዘባችንን ከፍለን እና ተጋብዘን ገባን ያሉት ተመልካቾች፤ ገንዘባችንም ጊዜአችንም ባክኖ አዝነን ወጣን ሲሉ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ አንዲት ወጣት ከእህቷና ከሌላ ሴት ጓደኛዋ ጋር ፊልሙን ለማየትና ለመዝናናት ገብተው እንደነበር ጠቅሳ በግብአተ ድምፁ መፋለስ አዝነው ፊልሙ ሳያልቅ መውጣታቸውን ተናግራለች፡፡ በግብዣ ካርድ ገብቼ ነበር ያለን ዋለልኝ ሥጦታው በበኩሉ፤ አልፎ አልፎ ካልሆነ ተዋንያኑ ምን እንደሚሉ አይሰማም ነበር፤ አስቀድሞ ዝግጅት ሳይጨርሱ ተመልካች ፊት መቅረብ በጣም ያሳፍራል ብሏል፡፡