የዚህ ነገር ጥሩ ጐኑ ምንድነው? ጐጂውና የማይጠቅመውስ? እንግሊዝኛ ቋንቋ ተመራጭ የሆነበት ወይም በሌሎች ላይ ይህንን ያህል ተእኖ ሊያሳድር የቻለበት ዓለም አቀፍ እውነታስ ምንድነው? እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ደጋግመው እየተነሱ ከተለያዩ አካላት የሚቃረኑና የሚደጋገፉ ምላሾች ሲሰጡም ይታያል፡፡ወቅትና አጋጣሚ ይዞት በመጣ ጉዳይ ላይ ከመጨቃጨቅና ከመከራከር ይልቅ ክስተቱን ለራስ፣ ለሕዝብና ለአገር እንዲጠቅም አቅደው የሚጠቀሙበት ግለሰቦችና ተቋማት አሉ፡፡ “TADYAS ETHIOPIA” በሚል ርእስ ተዘጋጅቶ በ2003 ዓ.ም የታተመው መሐፍ ለዚህ እውነት ምሳሌ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ መሐፉ ለልጆች እንዲደርስ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው የቀረበው፡፡
70 ገፆች ያሉትና በመሐመድ ሰልማን ተዘጋጅቶ ..ቃል.. የመፃሕፍት አሳታሚና አከፋፋይ ያሳተመው መሐፍ እንዲዘጋጅ ምክንያት የሆነው፤ ወላጆች በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀና ስለ ኢትዮጵያ የሚያወራ ለልጆች የሚሆን መሐፍ መጠየቃቸው እየበረከተ በመምጣቱ ነውም ተብሏል፡፡
በ6 ምዕራፎች ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታዎች፣ ዓመታዊ የሕዝብ በዓላት፣ ታዋቂ ሰዎች፣ አገሪቱን ስላስተዳደሯት ነገሥታት፣ ስለ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችና ባህላዊ ምግቦች የተወሠኑትን መርጦ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያቀረበው መሐፍ፤ ለልጆች ታስቦ ከመዘጋጀቱ ጐን ለጐን ..መሐፍ አንድ.. በሚል ቀጣይነት ያለው መሆኑን ጠቁሟል፡፡
መሐፉ ልጆች በቀላሉ ሊረዱት በሚችሉትና በሚስብ መልኩ ለማቅረብ ጥረት ተደርጐበታል፡፡ በየርእሰ ጉዳዩ ከሚቀርቡ ትረካዎች በፊት ልጆች (አንባቢያን) እንዲመልሱት የሚያበረታታ ጥያቄ ይቀርባል፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያ በዓለም ካርታ የት ቦታ ላይ እንደምትገኝ፣ የሚጐራበቷት አገራት እነማን እንደሆኑ፣ በአገሪቱ የሚኖረው ሕዝብ ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ... ጥያቄ አቅርቦ ነው ወደ ርእሰ ጉዳዩ የሚገባው፡፡
ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ወደቡ ያላቸውን ሦስት አገራት እንደምትጐራበት፣ ከዓለም ታላላቅ አገራት በ27ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ፣ የዓለም ዝቅተኛው የመሬት ክፍል በኢትዮጵያ እንደሚገኝ፣ ነፃነቷን አስጠብቃ የኖረች አገር ስለመሆኗ... ተተርኮ፤ ከቀረበው ሁፍ የተመረጠ ቃላት (vocabulary) እንዲያጠኑና የመሐፉ አንባቢ ልጆች በቃላቱ የየራሳቸውን ዐረፍተ ነገሮች እንዲሰሩ ያበረታታል፡፡
ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታዎች አንዱ ስለሆነው አክሱም የሚነበበው ሁፍ ከመቅረቡ በፊት ..አክሱም የሚለውን ቃል ስትሰሙ ምን ይታሰባችኋል?.. የሚል ጥያቄ የሚቀርብላቸው የመሐፉ አንባቢያን፤ ስለ አክሱም ከቀረበው ሁፍ ቀጥሎ ከታሪኩ የተውጣጡና ልጆቹ እንዲመልሱት የቀረቡ ጥያቄዎችም አሉት፡፡
mI¼û አክሱምን ጨምሮ ላሊበላ፣ ጐንደር፣ ሐረር፣ መቀሌ፣ ባሕርዳር፣ ሶፍ ዑመርን ሲያስተዋውቅ ከዓመታዊ የሕዝብ በዓላት ደግሞ የአዲስ ዓመት፣ የመስቀል፣ የገና፣ የጥምቀት፣ የፋሲካ፣ የረመዳንና የአረፋ በዓላት መቼ፣ በምን ዓላማና በምን መልኩ እንደሚከበሩ ያስተዋውቃል፡፡ በሦስተኛው ምዕራፍ ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን፣ አትሌት ኃይለ ገብረሥላሴን፣ አርቲስት አስቴር አወቀን፣ ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠንና ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን ያስቃኛል፡፡
ስለ ከበሮ፣ ማሲንቆ፣ በገና፣ ዋሽንት በምዕራፍ አምስት አቅርቧል፡፡ በመጨረሻው ክፍል ከኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ስለ እንጀራ፣ ገንፎ፣ ክትፎና ዳቦ ተፏል፡፡ ስለ እያንዳንዱ ዝርዝር መረጃ ለመስጠትም ተሞክሯል፡፡ ድፎ ዳቦ፣ ሐበሺት፣ አንባሻ፣ ሙልሙሉና ቂጣ የሚባሉ የተለያዩ የዳቦ አይነቶች እንዳሉና ከምን እንደሚዘጋጁ፣ በምን መልኩ እንደሚጋገሩ፣ ከየትኞቹ ሕዝብና በዓለ ጋር እንደሚያያዙ፣ መቼና ለምን አገልግለት እንደሚውሉ ተፏል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ለልጆቻችን ልንነግራቸው የሚገባን ስለሌሎች ሳይሆን ስለ አገራቸው ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባሕላዊ... ነገሮች መሆን አለበት የሚል መልእክት በጀርባ ገ ያሰፈረው ..ታዲያስ ኢትዮጵያ.. መሐፍ፤ አቀራረቡ በብዙ መመዘኛዎች አዲስ መሆኑንም ያመለክታል፡፡ በዚህም ምክንያት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ይወዱታል የሚል ሃሳብም አስፍሯል፡፡
መሐፉ ላይ ከታዩኝ ችግሮች ..መሐፉ ለአዲስ አበባ ልጆች ብቻ ነው እንዴ የተዘጋጀው?.. የሚያስብል የቴክኒክ ስህተት ተጠቃሽ ነው፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ስለ ጐንደር በሚያስተዋውቀው ሁፍ፤ በአሁኑም ዘመን በንጉሥ ፋሲል ግቢ ስለሚከበረው የጥምቀት በዓል ሲገለ “I am sure you have seen this in Jan-Meda while being colorfully celebrated” ይላል፡፡ ይህ ደግሞ መሐፉ ለአዲስ አበባ ልጆች (አንባቢያን) ብቻ የተዘጋጀ አስመስሎታል፡፡ የሆኖ ሆኖ በተያያዘ ከውጭ የሚመጡብንን ጫናና ችግሮች በዚህ መልኩ ለአገርና ሕዝብ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከሩ የሚደነቅ ነው፡፡