Saturday, 27 August 2011 12:50

ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት

Written by  ጤርጢዮስ - ከቫቲካን
Rate this item
(0 votes)

በእናት ሞት ሰበብነት የተነሰውና     ..የህይወት ትርጉም.. የተሰኘው የዋለልኝ እምሩ መጽሐፍ    ..ያልተመረመረ ህይወት ዋጋ የለውም.. (unexamined life is not worth living) የሚለውን የጥንቱን ፈላስፋ ሶቅራጥስ አባባል መነሻው አድርጐ ያልፈተሸው የህይወት መስክ የለም፡፡ ይህን ለማሳካት ደግሞ ሃይማኖትን፣ ፍልስፍናንና ሳይንስን በጥልቀት መዳሰሱ ግድ ነውና ያንንም በሚገባ አድርጓል፡፡ በአንትሮፖሎጂና በፍልስፍና የትምህርት ዘርፎች መመረቁም የመረጃ ብርበራውንም ሆነ የአቀራረብ ስልቱን ሳያቃኑለት አይቀርም መሰል የዘመናቱን የሰው ልጆች የህይወት ትርጉም ፍለጋ ታሪክ፣   322 ገጽ ባለው መጽሐፍ አሳጥሮና አሳምሮ ማቅረብ የቻለበት ጥበብ ድንቅ የሚሰኝ ነው፡፡

በሰከነና በበሰለ አቀራረቡ ምክንያት ቆይቶ የሚመጣው ብይኑ ምን እንደሆነ ለመጠርጠር እስኪቸግረን ሚዛኑን ለመጠበቅ ያደረገው ጥረትም ምሁራዊ ዲሲፕሊኑን ብቻ ሳይሆን ቅን ሰብዕናውንም የሚያመለክት ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ እነሆ እኔ ደግሞ ..ፈትኑ መልካም የሆነውን ያዙ!.. የሚለውን መለኮታዊ ቃል በምክንያት ዋቢ አድርጌ አባይን በጭልፋ እንዲሉ ዓይነት ከመጽሐፉ የጨለፍኩትን የህይወት ትርጉም ፍለጋ ለእናንተ ላቃምስ ነው፡፡
መጽሐፉ- የሰው ልጅ የህይወት ትርጉም መነሻ ጥያቄዎቹን ሥርዓት ባለው መንገድ ዕውቀት መገንባት ሲጀምር ከሚያነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች መካከል የህልውና ጉዳይ ዋና ሆኖ፣ አጠቃላዩን የህልውና መንስኤ በተመለከተም በፍልስፍና ዲበአካላዊ (metaphysical) በሆነ አመለካከት ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ማድረግ ጀመረ፡፡ በዚህ አቅጣጫ የአስተሳሰብ አድማሱን አስፍቶም ..የህልውና መሠረቱ ምንድነው? መኖር ወይም አለመኖር ራሱ ምንድነው?፣ በእርግጥ ፈጣሪ አለ ወይ?.. ብሎ መመርመርን አወቀበት፣ በሃይማኖታችን የማይጠፋ ህልውና የሸለምነው ሰው ፍጻሜው አፈር ከሆነ የመፈጠር ትርጉሙ ምንድነው? የሚሉት ጥያቄዎቹም ተገቢ ጥያቄዎች ሆኑ ይላል፡፡ ፈላስፋዎቹ ..ህይወት ትርጉም አለው.. ሲሉም ሆነ ..የለውም!.. ሲሉ ያቀረቡትን ምክንያት በስፋት ይዘረዝራል፡፡
መጽሐፉ የህይወትን ትርጉምና ዓላማ በጥልቀት መመርመር የተጀመረው በታላቁ ግሪካዊ ፈላስፋ ሶቅራጥስ (469-399 ከክ.ል.በ) እንደነበር ሲገልጽ የፍልስፍናው ዓለም የህይወትን ትርጉም የተረዳው በሁለት መንገድ ነው፡፡ በሁለንተናዊነቱ (universality) እና በአንጻራዊነቱ፡፡ የህይወትን ሁለንተናዊነት በተመለከተ ህልውናን በሁለት ዓለሞች ከፍሎ በመረዳቱ የሚታወቀው የሶቅራጥስ ተማሪ የነበረው ፕሌቶ (428-348 ከክ.ል.በ) ነው፡፡ ፕሌቶ የማይለዋወጡና ዘለዓለማዊ የሆኑ ፍም ነገሮች Ideas-Forms የሚኖሩበትን ዓለም ..የወዲያኛው.. ብሎ ሰየመው፡፡ ምጡቅነቱን (Transcendental) ለመግለጽም ያንን ዓለም “The world of Being” ሲለው ተለዋዋጭ ጊዜያዊና ፍምነት የሌላቸውን ቁሳዊ ነገሮች የሚኖሩበትን ዓለም ደግሞ “the world of becoming” በማለት ጠርቷቸዋል፡፡ የጀርመኑ ሃሳባዊ ፈላስፋ ጆርጅ ሄግልም (1770-1831 ዓ.ም.) በአመዛኙ ያተኮረው ከሰው አዕምሮ ውጪ ሆነው ራሳቸውን ችለው ስለሚኖሩ ፍም ሃሳቦች (Absolute Ideas) ሲሆን የነገሮችን የተናጠልና የወል ተፈጥሮ ዲያሌክቲካዊ ግንኙነት መሠረት በማድረግ ህልውና ትርጉም ያለው መሆኑን አስረድቷል፡፡ ይሁንና ግን የነዚህን ሃሳባዊ ነገሮች ህልውና ማረጋገጥ ስለማይቻል ለሰውም ሆነ ለሌላው የመኖር ትርጉም ናቸው ለማለት ማስቸገሩን ይገልጻል፡፡  
ከዚህ በተቃራኒ የቆመው የአንጻራዊነት (relativism) ፍልስፍና የሁለንተናዊነትን አስተያየት አይቀበልም፡፡ ከዚህ ፍልስፍና አራማጆች መካከል ሲንገር የተባሉት ፀሐፊ የተናገሩት እንዲህ ነው Y§ል- ..በህዋ ውስጥ ባሉ ነገሮች ሁሉ በተመሳሳይነት የሚገኝ አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም የለም፡፡.. በአጠቃላይም በዚህ ፍልስፍና አራማጆች ዘንድ የህይወት ትርጉም መሠረቱ ተፈጥሮም ሆነ ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ መንፈሳዊ ኃይሎች አይደሉም፡፡ ይልቁንም የሰው ልጅ የህይወት ትርጉም መሠረቶች ራሳቸው ሲሆኑ ለግለሰቦች ፍላጐታቸው፣ ምርጫቸው፣ ውሳኔያቸው፣ አመለካከታቸውና እምነታቸው የህይወት ትርጉማቸው ነው፡፡ ለዚህ አመለካከት አንኦት ሰጥተው የሚያቀነቅኑት ፈላስፎች ደግሞ ህልውናውያን (existentialist) ይባላሉ፡፡ የፍልስፍናው ጠንሳሽ የሆነው ዣን ፖል ሳርተር (J-P Sarter 1905-1980 ዓ.ም.) የህይወት ትርጉም የግለሰቦች የምርጫ ጉዳይ መሆኑን ለመግለጽ የሚከተለውን ስለማለቱ Y«QúL- ..የምንመርጠውን እንኖራለን፣ ደፋር መሆን ይቻላል፣ ፈሪም መሆን ይቻላል፣ የዋህ ወይም መጥፎ ሰዎች ልንሆን እንችላለን፤ የምንሆነው ግን የመረጥነውን ነው፡፡.. አንዳንድ ፈላስፎች ግን ግብን ከማሳካት በተጨማሪ የሥነ-ምግባር እሴቶች የህይወት ትርጉም ግብዓት መሆን ይቻላል፣ የዋህ ወይም መጥፎ ሰዎች ልንሆን እንችላለን የምንሆነው ግን የመረጥነውን ነው፡፡.. አንዳንድ ፈላስፎች ግን ግብን ከማሳካት በተጨማሪ የሥነ-ምግባር እሴቶች የህይወት ትርጉም ግብዓት መሆን እንዳለባቸው ይገልጻሉ፡፡ ይህን መሠረታዊ አመለካከት በዘመናዊው ዓለም በስፋት ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደረጉት ደግሞ ሰብዓውያን (Humanists) የሚባሉ ምሁራን ናቸው፡፡
የህይወት የመጨረሻ ግብ ምንድነው?
ፀሐፊው የህይወት ትርጉም ፍለጋውን በስፋት ቀጥሏል፡፡ እኔ ደግሞ መሠረታዊ ናቸው የምላቸውን ብቻ በጥቂት በጥቂቱ እየቆነጠርኩ ነው፡፡ የህይወት ትርጉምና ዓላማ እንደየግለሰቦች አመለካከት የተለያየ ነው፡፡ ትርጉም ያለው ህይወት ማለት ለአንዱ ችሎታውን አውጥቶ መጠቀም ሲሆን ለሌላው ፍቅርን መስጠትና መቀበል ነው፡፡ ለአንዱ ተጋጣሚን አሸንፎ ሥልጣን ኮርቻ ላይ መፈናጠጥ ሲሆን ሌላው ደግሞ የህይወትን ትርጉም ከገንዘብ ነጥሎ ማሰብ አይሆንለትም፡፡ ይህም ሆነ ያ ግን የፈለጉትን አግኝቶ ደስ መሰኘት የሰው ልጅ የህይወት ትርጉም ማጠንጠኛ ይመስላል፡፡ ለፈላስፋው አርስቶትል የህይወት መልካሙ ነገር (the highest good) ለብዙ ጊዜ እርካታን የሚያላብስ ደስታ ሲሆን መገኛው ግን ስሜትን ተቆጣጥሮና በህሊና (reason) እየተመሩ መኖርና በዓለም ውስጥ ስላለው የተፈጥሮ ሥርዓት በፍልስፍና ዕይታ በጥልቀት እያሰቡና እየተመራመሩ መረዳት መቻል ወይም የተመስጦ ህይወት (contemplative life) የደስታ ምንጭ ነው፡፡መጽሐፉ መነበቡን ቀጥሏል፡፡ በፍልስፍናው ዓለም ደስታን ከሁሉ ነገር በላይና የመጨረሻ የህይወት ግብ የሚያደርገው አመለካከት ተድላዊነት ወይም ሐሴታዊነት (Hedonism) ይባላል፡፡ ይላል፡፡ y..ሐሴታዊነት´ መነሻ የሆነው ሶቅራጥስ ቢሆንም ራሱን የቻለ የፍልስፍና ርዕስ እንዲሆን ያደረገው ግን የሴሬኒያን ፈላስፋዎች (cryonic) መሪ አሪስቲፐስ (435-356 ከክ.ል.በ) መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሐሴታዊነት ይበልጥ ስፋትና ጥልቀት ያገኘው በኢፒኩረስ (341-270 ከክ.ል.በ) ሲሆን የዘመናዊው ዓለም የዚህ አስተሳሰብ ዋና አቀንቃኞች ደግሞ ጀርሚ ቤንትሃም እና ጆን ስቶርት ሚል መሆናቸውን ይጠቁማል፡፡ ይሁን እንጂ የጥንቶቹ ፈላስፎችና ዘመነኞቹ አተያይ ለየቅል ነው፡፡ ይኸውም አሪስቲፐስ እና ኢፒኩረስ ደስታን ከግለሰቦች አንጻር ሲመለከቱ (egoistic hedonism) እንግሊዛውያኑ ደግሞ በግለሰቦች ተወስኖ የማይቀርና ሁሉ ሊካፈሉት የሚገባ ማኅበራዊ ደስታን (social hedonism) ናፋቂ ናቸው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፤ ግሪካውያኑ ሃሴታውያንም ቢሆኑ ግለሰባዊ ደስታ ራሱ ከየት ይመነጫል ለሚለው የሚሰጡት ትርጉም የተለያየ ነው፡፡ በዚህም መሠረት አርስቲፐስ ጥልቅ የሆነ ስሜታዊ ደስታንና ፈንጠዚያን በማስቀደም ..ብላ፣ ጠጣ እናም ደስ ይበልሀ ነገ ልትሞት ትችላለህና.. (Eat, Drink, and be Merry for tomorrow you may die) የሚል አንድምታ ያለው ሃሳብ ሲያራግብ፣ ኢፒኩረስ ደግሞ የአዕምሮ ሰላምን በማስቀደም የተሟላ ደስታ ለማግኘት ከአካላዊ ህመምና ከአዕምሮ መታወክ ነጻ መሆን እንደሚያስፈልግ ያስረዳል፡፡ (Freedom from pain in the Body and from trouble in the mind.)  ነው ይላል፡፡መጽሐፉ ስለነዚህ ብቻ ሳይሆን በተቃራኒው ..ደስታን መሻት የህይወት ትርጉም አይደለም.. የሚሉ ፈላስፎች እንደነበሩም ይነግረናል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከእነርሱ ትምህርት በማፈንገጥ ተቃዋሚ የሆናቸው ሔጌስያስ (300 ከክ.ል.በ) የተባለ ፈላስፋ ይገኛል፡፡ የተድላውያንን ሃሳብ በመተቸት ረገድ አንቲስተንስ (445-365 ከክ.ል.በ) እና ኢፒክትተስም (55-135 ዓ.ም.) ተቃራኒ አስተሳሰብን ስለማራመዳቸውና  ..የምንኖረው ደስታን ለማግኘት ነው.. የሚል የህይወት መመሪያ እንዳይኖር የሚያደርግ ትምህርት ይዘው ስለመቅረባቸው ይጠቁመናል፡፡ የዚህ ታሪክ አስገራሚው ክፍል ደግሞ ፈንጠዚያን የህይወቱ ግብ አድርጐ የወሰደው አሪስቲፐስ እና ከዚያ በተቃራኒ የተሰለፈው አንቲስተንስ በተመሳሳይ ወቅት ሁለቱም የሶቅራጥስ ተከታዮች የነበሩ ሲሆን ..በህይወት ዘመናችን ልናገኘው የሚገባ መልካም የሆነ ነገር ደስታ ነው፡፡.. በማለት ሶቅራጥስ የተናገረውን አሪስቲፐስ አካላዊ እርካታና ስሜታዊ ፈንጠዚያ አድርጎ ሲረዳው፣ አንቲስተነስ ደግሞ የአስተማሪውን ሶቅራጥስ የግል ህይወት በመመልከት ደስታ ማለት ለሥጋዊ ደስታ ሳይጓጉ፣ ተድላን፣ ክብርን፣ ምቾትን ወዘተ... ንቆ ራስን ገዝቶ መኖር ትክክለኛው የኑሮ ዘይቤና የህይወት ግብ እንደሆነ ተረዳ፡፡ የዚህ መጽሐፍ ፀሐፊ አቋምም ይኸው ይመስላል፡፡የህይወት ትርጉምና ግብ ደስታን መሻት ማድረግ የሚያስከትለውን ጣጣ በተመለከተም በመጽሐፉ የተነሳው የስቶይክ ፍልስፍና አራማጁ ኢፒክትተስ ገለጻ እንዲህ የሚል ነው- ..አዎን ህይወቴ ጠቃሚና ትርጉም ያለው የሚሆነው ደስተኛ ስሆን ነው፡፡ ደስተኛ የምሆነው ደግሞ እስካልተከፋሁና እስካልተጨነቅሁ ድረስ ነው፡፡ ብዙ የምመኛቸው ነገሮች Yñ‰lù- ሀብት፣ ሥልጣን፣ ውበት፣ ጤንነት ወዘተ... ሆኖም እነዚህ ነገሮች በእኔ ፈቃድና ውሳኔ ወይም ቁጥጥር ስር አይደሉም፡፡ እንደተመኘኋቸው መጠን ሁልጊዜም የማገኛቸው ነገሮች አይደሉምና፤ የተመኘኋቸውን ሳላገኝ የምቀር ከሆነ ደግሞ ህይወቴ ከደስታ ይልቅ በሀዘን የተዋጠ ይሆናል፡፡ ስለዚህም በቁጥጥሩ ስር ያልሆኑ ነገሮችን ከመመኘት መቆጠብ አለብኝ፡፡ በምኞት ውስጥ እንድገባ የሚያደርገኝን ፍላጐቴን መግታት ከቻልኩ ከእኔ ውጭ ያሉትን ነገሮች ተመኝቼ በማጣቴ የሚደርስብኝን ቁጭት፣ ሀዘን፣ መከፋት አስቀራለሁ፡፡..
ህይወት ትርጉም አለውን?
..የህይወት ትርጉም.. የተሰኘውን መጽሐፍ መሠረት አድርገን ፍለጋችንን እንደቀጠልን ነው፡፡ የሰው ልጆችን የጋራ ነገር ግን ልዩ ልዩ የስሜትና የዕውቀት ነብራቆችን በናሙና መልክ ወስደን እያየን ነው፡፡ አሁን የደረስንበት ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ከባዱም ይኸኛው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ..የህይወት ትርጉም ምንድነው?.. ለዚህ አስቸጋሪ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ፍለጋው እንደቀጠለ ቢሆንም ለአንዳንዶች ህይወት ትርጉም ያላት ስትሆን ለሌሎቹ ደግሞ አይደለችም፡፡ ይህ ደግሞ ከንቱና ምንም ቁም ነገር የማይገኝባት መሆኗን ማሰብን ያጠቃልላል፡፡ ለዚህ ደግሞ በዋናነት የሚያቀርቡት ምክንያት ዓለም በግፍ፣ በመከራና በስቃይ የተሞላች መሆኗን ነው፡፡ የመፍትሔ ሃሳቦቻቸውም ራስን መግደል፣ ተገቢ እስከማድረግ፣ ልጆችን ወልዶ ህይወትን እንዲቀጥል ማድረግን እስከመቃወም የሚዘልቅ ነው፡፡ ይህንን አስተሳሰብ ከሚያቀነቅኑት ፈላስፎችና ግለሰቦች ብዙዎቹ እግዚአብሔርN ህልውናውን መካድ የቀለላቸው ናቸው፡፡ የህይወትን ትርጉም አልቦነት አስቀድመው ከገለት ታዋቂ ፈላስፎች አንዱ አርተር ሾፕንሃወር (1788-1860 ዓ.ም.) ሲሆን ምክንያቶቹም ሁለት ናቸው፡፡ በግል ህይወቱ የደረሱበት ተደራራቢ ችግሮችና በዘመኑ የነበሩት ጦርነቶች ያስከተሉት ውድመት፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች የፈጠሩበት ሰቆቃ፡፡ ይህም ሆኖ ህይወት ትርጉም እንደሌላት የሚገልት አመለካከቶችም ሆነ የመፍትሔ አቅጣጫዎቻቸው ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ ለዚህ ዋነኛ አቋም ምስክሮች ሆነው የሚቆሙት ፍልስፍናዊ ዕይታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ህልውናዊነት (existentialism)፣ አውዳሚነት (nihilism) እና ህፀፃዊነት (absurdism) በነገር ዕይታቸውም ህፀፃውያኑ- ..ከተፈጥሮም ሆነ kእግዚአብሔር የሚገኝ ትርጉም ሊኖር ይችላል ነገር ግን ሰው በትክክል ሊረዳው የሚችለው አይደለም.. በማለት ከምክንያት ሲሸሹ ህልውናውያኑ ደግሞ ..ትርጉም የሚባል ነገር ቢኖርንኳ ትርጉሙ የሚመነጨው ከራሱ ከግለሰቡ እንጂ ከተፈጥሮ ወይም kእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለም፡፡.. የሚሉ ናቸው፡፡ ከነዚህ በጣም በተለየ መልኩ ሁሉም ነገር ከንቱ ስለመሆኑ የሚያውጀው አውዳሚነት የሚል ስም የወጣለት ፍልስፍና ሲሆን ለኒሂሊስቶች ትርጉም የሚባል ነገር ጨርሶ የለም፡፡ ነገሩ ከተፈጥሮም ሆነ kእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለም፡፡ ግለሰቦችም የራሳቸውን የህይወት ትርጉም ሊፈጥሩም ሆነ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን እነሆ የግለሰቦች የትርጉም አልባነት ችግር መፍትሔ ስለሌለው ትርጉም ፍለጋ መወራጨታችሁን አቁሙ የሚል ነው፡፡
ትርጉም አልባነትን በዚህ መልኩ እያስነበበን ያለው መጽሐፉ፤ የህይወት ትርጉም አልቦነትን በከፍተኛ ሁኔታ ካንፀባረቁት ፈላስፎች መካከል ፍሬድሪክ ኒቼን፣ (1844-1900 ዓ.ም.) አልበርት ካሙንና የህይወት ትርጉም የተሳሳተ አስተሳሰብ (illusion) ውጤት እንደሆነ የሚቆጥረውን yon-አዕምሮWN ምሑር ሲግመንድ ፍሩድን ትንታኔዎች በዝርዝር ያቀርባል፡፡ (ለእኔ ግን አንዳንዱን ትንታኔ የልጆች ጨዋታ ሌላውም በእርግጥም ዕብደት ይመስሉኛል የፍሩድ ጭንቅላት የተባለውን እግዜር እና ኒቼ የገደለውን እግዜር ማለቴ ነው) የሲግመንድ ፍሩድን ተወት አድርጌ ስለ ኒቼ የተጻፈውን ብጠቅስ ኒቼ ..ህይወት ትርጉም እንዲኖራት አድርጐ ያቀረበልን ሃይማኖት ስለሆነ መሠረቱ የሆነውን እግዚአብሔር መግደል ያስፈልጋል፡፡.. በማለት The Gay Science በተሰኘው የሥነ-ጽሐፍ ሥራው ላይ የዕብድ ገፀ-ባህሪ ባላበሰው ሰው አንደበት ..እግዚአብሔርN ገደልነው!፣ እግዚአብሔር ሞተ!.. በማለት ህዝብ የሚያከብረውንና ተስፋ የሚያደርገውን ማንነት አንቋሾ ገለ፡፡ ራሱን እንደ ክርስቶስ ተቃዋሚ (anti-christ) አድርጐ ለመቁጠር ያልፈራ ሰው ሆነ፡፡ (ሆኖም ኒቼ ከዕለት ዕለት የእውነት እያበደ ነበር፡፡)
የህይወት ትርጉም ከሳይንስና ከሃይማኖት አንጻር
..የህይወት ትርጉም.. መጽሐፍ ደራሲ የትርጉም ፍለጋውን እያሰፋ ሄዶ አሁን የደረስንበት ርዕስ ላይ አምጥቶናል፡፡ በሰቆቃ ውስጥ ያለውን የሰው ልጅ ነጻ ለማውጣቴ፣ ከአቅመ-ቢስነቱ ተላቆ ልዕለሰብነት ያለው ፍጥረት እንደሆን የሚያስችለው ዕውቀትና አቅም የት እንደሚገኝ እንድናስብ ብቻ ሳይሆን ተስፋችንን የት ላይ መጣል እንደሚገባን የሚነግረን ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሳይንስና ሃይማኖት ያላቸውን የነገር ዕይታ፤ የህዋውንና የህይወትን አፈጣጠር፣ የሞትን ምስጢርናእግዚአብሔርN ህልውና መፈተሽ አስፈልጐታል፡፡ ሳይንሱ የሚለውን ከሳይንስ ድርሳናት እግዚአብሔር የሚለውን ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር እያነፃፀረ ማሳየት ግድ ብሎታል፡፡ ለዚህ ንጽጽር መሠረታዊ ግብአቶቹ ደግሞ ከነዚህ ሌላ ሊሆን አይችልምና ሳይንስ በመረጃ (evidence) በሙከራ (experiment) ፣ ካላረጋገጥኩት፣ በአመክንዮ (logical Reasoning) ካልተረዳሁት የሚለውን የህዋና የህይወት መነሻ መሃፍ ቅዱስ በቀላል ቋንቋ ሁለቱም bእግዚአብሔር ይሁንታ መፈጠራቸውን፣ ሳይንስ እነዚህ ክስተቶች እውን ለመሆን ቢሊዮን ዓመታትን ሲጠራ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እነዚህ ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ዕውን መሆናቸው ስለመጥቀሱ ይጠቁማል፡፡ አብዛኞቹ ሳይንስ የሚመራባቸው አስተሳሰቦች እግዚአብሔር በፋክቱ ላይ ምንም ዓይነት አሻራ እንደሌለው ለማሳየት እየጣሩ ቢሆንም ስለህዋው አመጣጥም ሆነ ስለ ህይወት አፈጣጠር በሳይንሳዊ ዘዴ ለማስረዳት ያላቸው ዕድል እስካሁንም ፐርሰንቱ ዜሮ ከመሆን አልዘለለም፡፡ በሳይንሱ በኩል ዓለም ዕውን ትሆን ዘንድ በታላቅ ሙቀት ተፈጠረ የተባለው ታላቁ ፍንዳታም ሆነ ለፍንዳታው መንስኤ ሆናለች የተባለችው አንድ ወጥና የማትከፋፈል ቅንጣት (Singularity)  ወይም ቀዳማይ ቁስ (Primarily atom) ) ከየት እንደመነጩ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በምክንያትና ውጤት (Cause and effect) ቁሳዊ ህግ የማይዳኙ ህግ አልባ ፓርቲክሎች አተሞች መገኘትም ምንም እንኳ በኳንተም ፊዚክስ የነገሮቹ ባህሪ ሙሉ በሙሉ ከተፈጥሮ ህግ ውጪ እንዳልሆኑ ቢታሰብም ግን አሉ ሲሏቸው ስውር የሚሉ አፈንጋጭ ተፈጥሮዎች የሄስንበርግ የኢ - እርግጠኝነት መርህ (Heisenberg Uncertainty principle) በብዙ ሳይንቲስቶች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደረገ ነው፡፡ ይሁንና ..የህይወት ትርጉም.. ፀሐፊ እነዚህ ሁሉ እንቆቅልሾች ቆይተውም ቢሆን በሳይንስ መፈታታቸው አይቀርም የሚሉ ይመስላሉ፡፡ የህይወት አፈጣጠርንም በተመለከተ የሳይንሱ ጽንሰ ሃሳባዊ መላምት ህይወት የተገኘው በኬሚካል ንጥረ ነገሮች ግብታዊ ውህደት እንደሆነ ቢታመንም ..ግን ይህንን በቤተሙከራ (laboratory) ለመፍጠር የሚደረገው ሙከራ እንዲህ በአጭር ጊዜ የሚሳካ አይደለም.. የሚሉን ..የህይወት ትርጉም.. ፀሐፊ፤ አንዳንድ ተመራማሪዎችም ..ህዋሶች (Cells) ወደ ግዙፍ ውስብስብ አካል ከተለወጡበት ጊዜ ይልቅ የንጥረ ነገሮች ውህደት ወደ ህዋስነት የተቀየሩበት ጊዜ እጅግ በጣም ረጅምና ሂደቱንም ለመረዳት እጅግ አስቸጋሪ ነው.. ማለታቸውን፣ ማርጊዮልስ የተባለው ተመራማሪም ..አሚኖ አሲድ ወደ ባክቴሪያነት የተለወጠበትን ሂደት ከመረዳት ይልቅ ከባክቴሪያ ወደ ሰው ያለውን ለውጥ መረዳት ቀላል ነው.. ማለቱን ከነገሩን በኋላም እንኳ የነገውን የሰው ልጅ ተስፋ በዚሁ ሳይንስ ላይ ማረፉን የመጠቋቆም አዝማሚያ እያሳዩ መጥተዋል፡፡
እግዚአብሔር አለ ወይ?
አሁን ወደ መቋጫው እየተቃረብን ነው፡፡ ወደ ፀሐፊው ..ውሳኔ.. እየተጠጋን ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ህላዌ መጠየቅ ደግሞ የጥያቄዎች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ እነሆም ..የህይወት ትርጉም.. ፀሐፊ ስለ እግዚአብሔር ህላዌ የሚያቀርቡት ትንታኔና ግንዛቤ የሚከተለው ነው፡፡ ..ህልውና.. ለሚለው ቃል በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ አወዛጋቢ ያልሆነ ትርጉም ለመስጠት አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም በተለምዶ አንድ ነገር ህልውና አለው ስንል በተጨባጩ ዓለም ውስጥ ይኖራል፣ ከቦታና ከጊዜ አንፃር ሊገለጽ የሚችል ማንነት አለው ማለት ነው፡፡ በመጠን፣ ክብደት፣ ቁመት፣ ኃይል፣ ሙቀት፣ ቅርጽ፣ ቀለም፣ ሽታ ...ወዘተ ይታወቃል ማለት ነው፡፡ የዚህ ህልውና ዓይነት አረጋጋጮቹ ደግሞ የስሜት ህዋሳቶቻችን ናቸው፡፡ እውነታውን የስሜት ህዋሳቶቻችን በሚሰጡን መረጃና በአእምሯችን የመገንዘብ ችሎታ እስካልተረዳነው ድረስ ስለ ህልውና እርግጠኛ ልንሆን አንችልም፡፡
ሆኖም አንዳንዴ በስሜት ህዋሳቶቻችን መረዳት የማንችላቸውና ከላይ በዝርዝር ስለ ህልውና በሰጠነው ትርጉም መሠረት መግለጽ የማንችላቸው ነገር ግን ህልውና እንዳላቸው የምናምናቸው ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህ ደግሞ መንፈሳዊ ነገሮች ሲሆኑ እግዚአብሔር መላዕክት፣ ሠይጣን ብለን ልንረዳቸው እንችላለን፡፡ ሆኖም ጥናታችንን እግዚአብሔር ላይ ስናተኩር መጽሐፍ ቅዱስ ..እግዚአብሔርN ማንም አላየውም.. ስለሚል መኖሩን የተቀበልነው በእምነት ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ያወቅነው ተገልጦልን ወይም በተለየ ሁኔታ ድምፁን ሰምተን ሳይሆን በእምነት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ እምነት ደግሞ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ስለመሆኑ በዕብራውያን 11፤1 ላይ ተጽፏል፡፡ ስለዚህ እምነት በራሱ የህልውናው አረጋጋጭ ሆነልን ማለት ነው፡፡ በእምነት ..እግዚአብሔር አለ.. ስንልም ልክ አይተንና ሰምተን፣ ዳስሰንና ቀምሰን፣ ወዘተ ህልውናቸውን እንደምናረጋግጣቸው ነገሮች እግዚአብሔርም በእርግጥ ..አለ.. ማለታችን ነው፡፡ ሆኖም ከዚህ በተለየ መንገድ እግዚአብሔርN ሰዎች ያወቁት በእምነት ብቻ ሳይሆን በመገለጥም  ጭምር ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ በመገለጥ የተገኘ ዕውቀት ደግሞ በእምነት ብቻ ..አለ.. ከምንለው ይለያል፡፡ ለማንኛውም በሃይማኖት yእግዚአብሔር ህልውና ለመረጋገጥ ሁለት የተለያዩ መንገዶች መኖራቸው ግልጽ ነው፤ እምነት እና መገለጥ፡፡
ብያኔ ወይም ውሳኔ
በዚህ ርዕስ ሥር የሚቀርቡትና ለ..ህይወት ትርጉም.. ፀሐፊ ውሳኔ ሰበብ የሆነውን ሀሳብ ሳነሳ አንጀቴ እየተላወሰ ነው፡፡ መጽሐፉን ባነበብኩትም ጊዜ እንዲሁ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ የፀሐፊው ቀጥሎ የሚመጣው ብይን መንደርደሪያ ይህም ሁሉ ሆኖ ..በእርግጥ እግዚአብሔር አለን?.. የሚል ይመስላል፡፡ በእርግጥ ያለ ከሆነ ስግደታችን፣ ፀሎታችን፣ ፆማችንና ዝማሬያችን በእርግጥም ተመልካችና ሰሚ አለው ማለት ነው፡፡ ግን ካልሆነስ? በዚህ መሐፍ ውስጥ ለእንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ መልስ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው ወገኖች ምሥክርነት ቀርቧል፡፡ ሆኖም የዚህ መሀፍ አቅራቢ መነሻው ምን እንደነበር ግል ነው፡፡ ስለዚህም በርትራንድ ራሰል ሰዎች እግዚአብሔርN ማመን በመተውና ራሣቸውን በመተማመንና ዕውቀታቸውን በማስፋት እንቆቅልሻቸውን ይፈቱ ዘንድ በሞገተበት ሎጂክ ሳይሸነፍ አልቀረም፡፡
ሙግቱም bx„ ይህ ነው:- ..እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ የሚችል ከሆነ ለምን የዓለም ህዝብ በስቃይ ይኖራል? ሁሉን የሚችል ሆኖ ይህን ማድረግ ካልፈለገ ግን ርህሩህ አይደለም፤ እግዚአብሄር ሁሉን ያውቃል ከተባለ ለምን የዓለም ህዝብ በስቃይ ይኖራል? ስለዚህ ሁሉን አያውቅም ወይም ችግሩን ለማቆም አቅም የለውም ማለት ነው፡፡..
በእናቱ ሞት የተሳቀቀው የዋለልኝ እምሩ ልቦናም በዚህ የተፈተነ ይመስላል፡፡ ዓይኖቹን ሙሉ በሙሉ kእግዚአብሔር ላይ አንስቶ ወደ ሳይንስ እንዲያዞር ያስገደደ ከባድ ፈተና ገጥሞታል፡፡ በእምዬ ሞት ልቡ ተከፍቷልና ሚሊዮን ዓመታትን እንኳ ቢፈጅ የሰው ልጆች ሞትን እንኳ ድል የሚነሱበት የዕውቀት ልክ ላይ ይደርሣሉ የሚልን ተምኔታዊ ሃሳብ ማሰቡ ከመከፋቱ እንጂ ከምክንያታዊነቱ የፈለቀ የማይመስለኝ እንዲህ በማለቱ ነው:- ... . . ኑሮዬ፣ ተስፋዬ፣ መመኪያዬ፣ ኩራቴ፣ የመኖሬ ዓላማና የደስታዬ ምን የሆነችውን እናቴን ሞት አሣጣኝ፡፡
ለእንደዚህ ዓይነት እጅግ መራራ ሀዘንና አስከፊ ህይወት እንደማይዳርገኝ እተማመንበት የነበረው እግዚአብሔር በእንባ የተሞሉ ዓይኖቼንና bNqT ይንቀጠቀጥ የነበረውን ሰውነቴን አይቶ አልራራልኝም፡፡.. እንግዲያውስ በዚህ የ..ተቀጠቀጠ ሸንበቆ.. ላይ ሊያርፍ የሚገባው የሰው በትር የለም፡፡ የእኔም ምኞትና ፀሎት እግዚአብሔር በእርግጥ በሁሉን ቻይነቱ አለና የተሰበረው ልቡ በእርሱ ተጠግኖ በሌላ ሥራው አገኘው ዘንድ ብቻ ነው፡፡

 

Read 2861 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 13:00