...ሀኪሞቹ ብልሀቱ ገባቸው፡፡ ውሀ ፈልቶ በቂ ይንተከተካል፡፡ /ውስጡ ሊኖር የሚችለው በሽታ እንዲጠፋ/ ውሀውን በመርፌ መድሀኒት አስመስለው ይወጉዋቸውና፣
ኋየታዘዘልህን ኪኒን እንደተባልከው ካልዋጥክ ግን መርፌው ብቻውን አይሰራም፣ ይረክሳል.. ይሉዋቸዋል፡፡ /ይሄ psychology /ስነ ልቦና?/ ይባላል/
•የፈረንጅ ስምና የፈረንጅ መድሀኒት ያላቸው በሽታዎችም ይይዙን ጀመር፡፡
ለነገሩ በሽታዎቹ እነዚያ ድሮ የምናውቃቸው አንጡራ ሀብታችን ናቸው፡፡ ፈረንጅ ሀኪም ሲያስከትሉ ጊዜ እንግዳ መሰሉንና ወረት መሳይ ሆኑ፡፡ የዘመኑ ፋሽን.. ከስማቸው ጋር ገና ያልተዋወቀ ፋራ ሆነ፡፡
የህዝብ ማመላለሻ ከባድ መኪና ቴፕ - ሪኮርደሩን በድም ማጉያ እያስጮኸ ሲጓዝ፣ ወበቁ ያፈነው ተሳፋሪ መስኮት ሊከፍት የሞከረ እንደሆነ ኋኩራን ዴር ልታስመታን ነው..?.. ብለው በድምፃቸው ያካልቡታል፡፡ ይሄ ሁሉ የስልጣኔ ምልክት ሲከሰት የሾፌሩ ረዳት ደረቱን ለነፋስ ሰጥቶ ሲሄድ ለምን ኩራን ዴር አይከረብተውም? ሾፌሩንስ? ይህን መጠየቅ ፋራነት ነው፡፡
አንዳንድ ወይዛዝርት ፊታቸው በህመም ተኮማትሮ እያስገሳቸው ኋወይ ፈጣሪዬ.. ደሞ ያቺ ጋስትሪኬ ተነሳችብቃ.... ይላሉ፣ በድምፃቸው ቅላፄ ትልቅ ብዙ ጉራ እየነፉ፡፡ አልፎ አልፎ አንድ ነጭ ኪኒን ይውጣሉ [wNìCM ያው ናቸው፣ የፆታ ልዩነት አያረጉም በሽታዎቹ]
ብዙዎቻችን በነዚህ ዘበናይ በሽታዎቻችን እንኮራለን፡፡ allergy የሚባለው በሽታ ግን ታማሚውን በማፈን ትንፋሽ እየከለከለ ተመልካችን ጭምር ስለሚያሰቃይ፣ በሽታው ፋታ በሚሰጣቸው ጊዜያት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ጓደኞቻቸውም የተኩራራ ጉራ ይነዙበታል፡፡
/..እንዲህ ብታየቃ መስዬህ ድሀ
ያማቶቼ ቤት ባለጉልላት.... ብሎ፣ ቤት ሳይመታ የገጠመውን የድሮ ሰው ደስታ ያስታውሰናል፡፡/
ሁለት
እነዚያ ባለፈው እትማችን ወጣቶች ሆነው በአማላጅ፣ በደብዳቤ፣ በመሀረብ ይገናኙ የነበሩት ወጣቶች፣ አድገው ለወግ ለማዕረግ ደርሰው የበሰሉ ዜጋዎች ሆነዋል፡፡ ጮሌ ሴት አዋይም፣ አቃጣሪም፣ ብርችንችንም፣ የአባለ ዘር ኋበሽታና መድሀኒትም.. ይበዛል ማለት ሆነ፡፡
ከሁሉ አስደንጋጭ በሆነው እንጀምርና፣ ከቅዠት የባሰ ሲኦል ይመስላል ከነስሙ፡፡ ኋባምቡሌ.... በወሬ ነው እንጂ ባምቡሌ የያዘው ሰው አናውቅም፡፡ ብብትህ ስርና ጭንህ ስር ትንሽ እ መስሎ ይጀምርና፣ እያበጠ ይሄዳል፣ በዚያ መጠን ስቃይህ ይጨምራል፡፡ ስድሳ ሻማ አምፑል ሲያክል ጩኸትህ አውራ መንገድ ድረስ ሰው ያውካል፡፡ ክንዶችህና ጭኖችህ ተበርግደው ተከፍተው ጭራቅ እንቁራሪት ትመስላለህ፣ እብጠቶቹ ተራ በተራ ፈንድተው ሞት እስኪገላግልህ ድረስ፣ ይባል ነበር እንግዲህ፡፡
በነገራችን ላይ፣ የአባለ ዘር በሽታ ሲባል በመጀመሪያ ሲከሰት ገዳይ ነበር፡፡ ግን አንዳንድ እድለኛ ሰዎች አሉ፣ በሽታው አይነካቸውም፡፡ እንዴት እንደሆን እንጃ፣ ያ ገዳይ የነበረው በሽታ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ፣ ጉልበቱ እየደከመ ሄዶ የድሮ ጨዋታ ይሆናል፣ ተረት ተረት እየሆነ ይሄዳል፡፡ ለምሳሌ ጨብጥ /ጨብጦ/ በአፍላ እድሜው ዘመን ቢሆን ሲይዝህ ፊኛህ ሞልቶ ወጥሮህ በፍጥነት ሽንት ቤት ትገባለህ፡፡ እያማጥክ ብትገፋ አንድ አምስት ጠብታ ብቻ ነው የሚወጣህ፡፡ እንደ ምግል ዓይነት ነገር በየጥቂት ደቂቃው ጠብ እያለ ይወጣል፡፡ በህመም ትጮኻለህ፡፡ ስንት ቀን ወይ ሳምንት ተሰቃይተህ እንደምትሞት እንጃ፡፡ ትውልዶች እያለፉ በሽታው እየተዳከመ ሄደ፡፡
ከዛሬ ሀምሳ ዓመት በፊት ጨብጦ የያዘው ሰው ኋጉንፋን ይዞኛል.. ነበር የሚለው፡፡ ምክንያቱም penicillin ኪኒን እየዋጥክ ከግብረ-ስጋ ሁለት ሳምንት ብቻ ከተቆጠብክ ትድናለህ፣ ኋየፔኒሲሊን ፈጣሪ Sir Alexander Fleming ዘሩ ይለምልም....
አለላችሁ ደሞ አቶ ከርክር.. እሱንም እንደ ባምቡሌ በወሬ ወሬ እናውቀዋለን እንጂ የያዘው ሰው አላጋጠመንም፡፡ /ቢያጋጥመን ኖሮ ግን ለዚህ ጽሑፋችን መልካም መረጃ ይሆን ነበር፤ አልሆነም እንጂ/ ስሙ እንደ¸ያመለክተው የመሳርያህን ጫፍ ይከረክረዋል፡፡ እኛ ስንሰማ ታካሚው ሀኪም ጋ የደረሰው ጫፉ ካሁን ካሁን ሊበጠስ ሲል ነበር፡፡
ሀኪም ሱሪውን አስወለቀውና ኋእውነትም ከርክር ነው.. አለው ኋእስቲ ዝለል.. ዘለለ፡፡ ኋአሁንም.. ዘለለ፡፡ ጫፉ ረገፈ፣ ተንከባለለ፡፡
ሀኪም ጓንቲ ባደረገ እጁ አንስቶ ኋልጣለው ወይስ ለማስታወሻ በኤንቨሎፕ አሽጌ ልስጥህ? ወይስ ወስደህ በሙጫ ታጣብቀዋለህ? ወይስ. . ...
ኋኧረ ይስጡይ.... አለ ባለ ንብረት እየነጠቀው ኋባይሆን ለጠንቋይ እሸጠዋለሁይ..
ኋየሚገዛህ አታገቃም አትልፋ፡፡ እኔም እሚገዛቃ አጥቼ ነው ጫፌን በፀሐይ አድርጌ ቋንጣውን በብርሌ አልኮል ውስጥ አሽጌ ያኖርኩት..
አሁን እነሆ ወደ ዋናው እንግዳችን ወደ ቂጥቃ ደረስን፡፡ ጥንት በገዳይነት ዘመኑ ሁለት ዓይነት ነበረ፡፡ ምስሬ ቂጥቃ እና ማጭዴ ቂጥቃ ይባላሉ፡፡ ምስሬው ፊትህን ምስር የተበተነበት ያስመስለዋል፡፡ ብዙ ትሰቃያለህ እንጂ አትሞትም፡፡ ማጭዴው ግን ክፉ ነው፡፡ አእምሮህ ላይ ይወጣል፡፡ ማበድህ እየታወቀህ ታብዳለህ፡፡ አብደህም አትቀር፣ ይገድልሀል፡፡
በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የኖረው ድንቅ የአጫጭር ልቦለድ ደራሲ Guy de Maupassant በቂጥቃ ያበደ ጊዜ Le Horla የሚባል፣ እንደ ቅዠት የሚያስፈራ አጭር ልቦለድ ጻፈ፡፡ Le Horal ፈረንሳይኛ ኋል አይደለም፤ የእብደቱ ስም ነው/ እንዲህ ይጀምራል፡-
ኋስትተኛ አንድ ጠርሙስ ሙሉ ወተት ጠረጴዛው ላይ ትቼ ነበር፡፡ ጧት ስነሳ ግማሽ ጠርሙስ ብቻ አገኘሁ፡፡ እዚች ክፍል ውስጥ ብቻዬን ነው እምኖረው፡፡ Le Horla ጠጥቶብቃ መሆን አለበት. . . ...
. . .ቂጥቃን እላይ ከተጠቀሱት በሽታዎች የሚለየው የሴቶች ሆኖ መወራቱ ነው፡፡ ሌሎቹን በወንድ ላይ ሲደርሱ ነበር እምንሰማው፡፡ ይሄኛው ግን ውበትና ግርማ ሞገስ ይኖረዋል /ገዳይነቱ ድሮ ቀርቶ አሁን ወረት ወይም fashion ሆኗል፣ እየተሽሞነሞኑ የሚመኩበት፣ እየተሽቀረቀሩ የሚንቀባረሩበት፡፡/
የቂጥኛም ልጅ ውርዴ ትባላለች፣ የደም ገምቦ እና ተጨማሪ ምስራዊ ቅመም መሳይ ነገር፡፡ የውርዴዋ ልጅማ እንደ ፀሐይ የሞቀች እንደ ጨረቃ ያማረች..
ቂጥቃ ማውጣት fashion ነው፣ ይወዳደሩበታል፡፡ አንዷ የበላይነቷን ለሌላዋ ለማሳየት፣ አንድ እጇን ወገቧ ላይ ጣል አድርጋ አንገቷን እያወዛወዘች፡- ኋአንዴ ቂጥቃ አወጣሁ ብሎ መንቀባረር ምንድነው? እኛ ሦስቴ ያወጣነውም እንዳንቺ አልተንቀባረርን እቴ.. ንገሩኋ ባይ....
ሦስት
መድኃኒት ያልተገኘላቸው በሽታዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ወደፊት ይገቃላቸዋል ብለን እናምናለን፡፡ Ralf Waldo Emerson አሜሪካዊው ፈላስፋ ስለ እፀዋት እንዳለው “And what is a weed but a plant whose virtues remain to be discovered?” /አረም ምንድነው? ጥቅሙን ገና ያላወቅንለት እ አይደለምን?/
መድኃኒት ከታጣላቸው በሽታዎች ሁሉ በብዛት የሚታየው እብደት ይባላል፡፡ ብዙ ፈረንጅ እብዶች ናፖሊዮን ነቃ ይላሉ፡፡ ያገራችን እብዶች ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ነቃ ይላሉ፡፡ ጃንሆይ አማኑኤል ሆስፒታልን ሲጎበኙ አንዱ እብድ ማን እንደሆኑ ጠየቃቸው ይባላል፡፡ ሲነግሩት ኋእውነትም አብደሀል.... አላቸው ኋእፊትህ ቆሜ እያናገርኩህ አንተ ነቃ ትለኛለህ?.... አላቸው፡፡ /እና እሳቸው ኋእሱ ነው እኛን የሆነው? ወይስ እኛ ነን እሱን የሆንነው? ወይስ ምን?.. ብለው ያስቡ ይሆን አንዳንድ ጊዜ?/
ይህ ሰው ስላበደ ዘመዶቹና ወዳጆቹ ያዝናሉ እንጂ፣ እሱ በበኩሉ ተደስቶ የሚኖር ይመስላል፡፡ የተጐዳውስ ትንሽ ጠጠር ነቃ ብሎ ስላመነ፣ ዶሮ ብቅ ስትል ኋካየችቃ ትውጠኛለች.. እያለ መግቢያ የሚጨንቀው ሰውዬ ነው..
እብደት እንደየአገሩ ታሪክ፣ ባህልና ዘመን ይለያያል፡፡ አንዳንድ ናሙና እንመለከታለን፡፡
ሀ/ Howard hughes የሚባል genius በ1950ዎቹና 60ዎቹ በሆሊውድ የተደነቀ ፕሮድዩሰር እና ዳይሬክተር ነበር፡፡ እንዲሁም መሰሎቹ ያደነቁት ace pilot /ማለት ወደር የማይገቃለት/፡፡ ፊልሞቹ ውስጥ fighter bomber አሮፕላን በሚታይ ጊዜ እሱ ራሱ ነው የሚነዳው፡፡ ከምር..
እና የዚህ ጀግና እብደት ምን ነበር? በሽታ የሚያስተላልፉ germs የሚባሉ ነገሮች እንዳይጋቡበት መጠንቀቅ!ስለዚህ እቢሮው ውስጥ መሸገ፡፡ ሥራውን የሚያካሂደው በቴሌፎን ብቻ ሆነ፡፡ አንድ ታማቃ ቀቃ እጅ የሆነ private secretary አለው፡፡ ጉዳዩ እሱ ራሱ እንዲመለከተው የሚያስፈልግ ከሆነ /ለምሳሌ ሰነድ መፈረም/ ልዩ ፀሐፊው በስልክ ካስፈቀደው በኋላ disinfectant (germ ገዳይ/ መድኃኒት ከተረጨበት በኋላ ነው ወደ ቢሮው የሚገባው፡፡
ቀኗ መድረሷ እንደማይቀር ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ እንድያም ቢሆን. . .
ለ/ ሥልጣንና እብደት ተቆራቃቶ ሲከሰት ደግሞ ይኸውላችሁ፡፡ Haiti የምትባል ደሴት /የፈረንሳይ ቅቃ ግዛት የነበረች/ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ Papa Doc ይባላሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለሆኑ ህዝባቸው ወደ ቤተ መንግሥታቸው አቅጣጫ እየሰገደ ኋአባታችን ሆይ.. የምንለውን ፀሎት እንዲህ ያዜማል፡-
ኋአባታችን ሆይ፣ በቤተ መንግስትዎ የሚኖሩ ስምዎ ይቀደስ፣ መንግሥትዎ ይምጣ የእለት እንጀራችንን ይስጡነ ዛሬ. . ... ብታምኑም ባታምኑም አንባብያን ሆይ፣ Papa Doc ሞቱ..
እና አልጋ ወራሻቸው Baby Doc ነገሰ.. እሱም “Baby Doc ሆይ፣ በቤተ መንግሥት የምትኖር. . ... እያሰኘ ጥቂት ወራት አስፀለያቸው. . .
. . .እና አንድ ቀን ገንፍሎባቸው ተነስተው ደብድበው ረግጠው ገድለው ቦጫጨቁት.. ኋመካር የሌለው ንጉስ፣ ያለ አንድ ዓመት አይነግስ.. የሚባለው የአበው ተረትና ምሳሌ ከዚያ የተወሰደ ነው፡፡
ሐ/ አሁንም የስልጣንና እብደት ሌላ መልክ ይኸውላችሁ፡፡ b÷lÖn!ያለ!ZM ዘመን ኮንጐ የምትባለው የአልማዝ አንደኛ አምራች አገር የንጉሥ ሊዮፖልድ (King Leopold) የግል ንብረት ነበረች፡፡ /የአገሩ የቤልጅም ቅቃ ግዛት አይደለችም ማለት ነው/
ሂትለር የሚባለው እብድ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ለኩሶ የኤውሮፓ ዋና ከተማዎች በቦምብ ከፈራረሱ በኋላ፣ Mobutu Seseseko የሚባል እብድ የኮንጎ ፕሬዚደንት ሆነ፡፡ ባለ ሙሉ ሥልጣን.. እና የገዛ አገሩን እየበዘበዘ ስዊስ ባንክ ውስጥ ሃያ ቢሊዬን ዶላር አከማቸ፤ በግል ስሙ..
ይህ ሁሉ በሚሆንበት ዘመነ ሞቡቱ የኮንጎ መንግሥት የበጀት እጥረት ደረሰበት፡፡ አርባ አምስት ሚሊዬን ዶላር ብቻ..
ፕሬዚደንት ሞቡቱ ባንድ ዓመት የሚከፈል ብድር ተጠየቀ፡፡
እምቢ አይልም መሰላችሁ? ምክንያቱስ?
ኋምናልባት ከዚያ በፊት የሞትኩ እንደሆነ፣ ያበደርኳችሁን ለወራሽ ልጄ እንደምትከፍሉት እርግጠኛ መሆን እንዴት እችላለሁ?.. አላቸው. . .
መ/ ገንዘብ ሌላ የማይድን እብደት ነው፡፡ ግን ከልጅነታችን ጀምሮ አብሮን ይኖራል፡፡ በብዙሀን መገናኛ በርቀትም በቅርበትም ልንከታተለው እንችላለን፡፡
ሰው የሚመገበው፣ የሚለብሰው፣ የሚጠለልበት ያስፈልገዋል፡፡ ምቾትንና ዘላቂነትን እንጨምርበት፡፡ ለአንድ ሰው አንድ ሚሊዮን ብር አይበቃውም? እሺ አሁንም ስንጨምርለት በዶላር ይሁንለት፡፡ አይበቃም?
ግን እዚህ አዲሳባ ውስጥ ብቻ እንኳ ብንወሰን፣ ስንትና ስንት ሚሊየኔሮች አሉ?.. ሲሞቱ አብሯቸው ላይሄድ፣ ይሄ ሁሉ ራሱን እያባዛ የሚሄድ ሂደት መሆኑን እየተገነዘብንላቸውም ቢሆን የማይድን እብደት ነው....
ሠ/ ይሄኛውና ሌላ እብደት፣ አብረነው በማደጋችን እብደት መሆኑን ሰው ካልነገረን አንገነዘበውም እንጂ፡፡ እሱ ራሱ ግን ሁልጊዜ ሲነግረን ኖረናል፤ በየቋንቋው፣ በየማቀንቀኑ፣ በየተረቱ፣ ኋበፍቅርሽ አበድኩልሽ.. I’m crazy about you! I’m crazy in love with you...
አራት
ሀ/ የፍቅር እብደት ውስጥ አማልክቱም አሉበት፡፡ የጥንት ሮማ ኮሜዲ ተውኔት Catullus የተባለ አርቲስት የጻፈው፣ ፍሬ ሀሳቡ እንዲህ ይላል፡፡
የፍቅር አምላክት Venus እና ቀልደኛ ህፃን ልጇ Cupid ለአማኞች አንደኛ ኋድንግል ምስለ ፍቁር ወልዳ.. ናቸው፡፡
አንድ ቀን ቬኑስና ክዩፒድ ወደ ሰዎች መኖሪያ ወረዱ፡፡ ክዩፒድ ሲጫወት ቀስቱን አንስቶ አንድ ፍላጻ አስፈነጠረ፡፡ አይስትም መቸስ፣ የአንዲቱን ውቢት ልብዋን በሳት፡፡ አይቀርላትም የታወቀ ነው፣ መጀመሪያ ካየችው ፍጡር ጋር ፍቅር ይይዛታል፡፡ እና ዓይኖቿ ተወርውረው አንድ ወደል አለሌ አህያ ላይ አረፉ፡፡ እንግዲህ ውቢቱ ምን ታድርግ? ምንስ ትሁነው? ለአንባቢ ምናብ እንተወዋለን. . .
ለ/ አሁንስ ለለውጥ ያህል፣ ወዲያውም ዓለም አቀፍ international universal ሆነን እንድንደሰት ወደ ጥንታዊት ቻይና ብቅ እንበል፡፡ በዚያን ዘመን ምትሀትና ተአምራት ይከሰታል፡፡
ንጉስ ድንቅዬ ተአምር መሳይ ቤተ መንግሥት አሳነ፡፡ ወደሰ tqds በዚህ ተዓምር የተመሰጠ ሰአሊ ይህን ቤተ መንግሥት ሰፊ ግድግዳ ላይ life-size ስእል ፈጠረ፡፡ ቤተ መንግሥቱን በመስተዋት እንደማየት ነበር..
ንጉስ ተቆጡ፡፡ ኋእንዴት አባክ ደፍረህ ቤተ መንግሥቴን ዓይኔ እያየ ትዘርፈኛለህ አንተ እርኩስ.... ብለው፣ እንዳይለምደው ዓይኑን አፈሰሱት፡፡
አንደኛዬን እርግጠኛ ልሁን ብለው ያሰቡ ይመስል፣ የቤተ መንግሥታቸውን ፈጣሪ አርክቴከት ኋእንዲህ ዓይነት ተአምር እንዳትደግም እናረጋግጥ.. ብለው አሳወሩት..
እንኳንም በዚያን ዘመን አልተፈጠርን..
እስከሚቀጥለው ቸር ይግጠመን አሜን..