Monday, 10 April 2017 10:30

በላይ አብ ሞተርስ ለሁዋዌ የመኪና ኪራይ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

    በላይ አብ ሞተርስ ከሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው የመኪና ሊዝ ስምምነት መሰረት፤ ዛሬ 36 ፒክ አፕ የመስክ ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
የኮርፖሬት የመኪና ኪራይ አገልግሎት በመጀመር በላይ አብ የመጀመሪያው እንደሆነ የጠቀሱት የድርጅቱ ኃላፊ፤ በተለያየ ምክንያት በራሳቸው ትራንስፖርት ከመጠቀም ይልቅ አገልግሎቱን ከአጭር ሳምንት እስከ ብዙ ወራት ለሚፈልጉ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የመስክ ጥናትና ምርምር ለሚያከናውኑ ተቋማት፣ የኢንቨስትመንት ቅኝት ወይም ጥናት ለሚያካሂዱ ባለሀብቶች፣ ለሕዝብ ቆጠራና ምርጫ … እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
የመኪናዎቹ አሽክርካሪዎች የበላይ አብ ሞተርስ ቅጥረኞች ሲሆኑ ተግባር ተኮር ስልጠና የተሰጣቸው፣ መኪኖቹም የደህንነትና የስምሪት ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ እንዲቻል ሲም ካርድና ጂፒኤስ ኤስ የተገጠመላቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሀገራችን የተንቀሳቃሽ ኔትወርክ ደረጃን ለማሻሻልና ለማሳደግ የሚሰራው ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ኢትዮጵያ፤ ከበላይ አብ ሞተርስ ጋር በገባው የሦስት ዓመት ውል መሰረት ፒክ አፕ መኪኖቹን በአዲስ አበባና በክልሎች ለትራንስፖርት አገልግሎት ይጠቀማል፡፡    
በላይ አብሞተርስ FAW  አውቶሞቢሎች ZNA ፒክአፕና ስቴሺንዋገን፣ አውቶቡሶችና ሞተር ሳይክሎችን አዳማ በሚገኘው የመኪና መገጣጠሚያ እየሠራ ሲሆን ባለሁለት ባለ አንድ ጋቢና ፒክ አፕ፣ ቀላል የጭነት መኪኖችን፣ ሚኒባስ፣ ከ22-45 መቀመጫ ያላቸውን ባሶች፣ ሎደሮች፣ ኤክስቫተሮች፣ ዶዘሮች፣ ግሬደሮች፣ ሮለሮችና የእርሻ መሳሪያዎችን ከውጭ ያስገባል፡፡

Read 5782 times