በተቃዋሚ አመራሮች እስር... መንግሥትና ተቃዋሚዎች የተወዛገቡ ነዉ
በተቃዋሚ አመራሮች እስር... መንግሥትና ተቃዋሚዎች የተወዛገቡ ነዉ
ባለፉት ሦስት ወራት መንግሥት በሽብርተኝነት ጠርጥሯቸው ከተያዙት ሠላሳ ሰዎች ውስጥ አስሩ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንደሆኑ ታውቋል፡፡ መንግሥት በሰጠው መግለጫ፤ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተያዙት እየፈፀሙ ያሉትን ተግባር ደርሼበት እንጂ በፖለቲካ ተሳትፎአቸው አይደለም ብሏል፡፡
በአዲሱ የውድድር ዘመን
ደሞዝ አድጓል፤ የተጨዋች 3ሺ የአሰልጣኝ 20ሺ ብር
-ክለቦች በፊፋ ደንብ መገደድ ይጀምራሉ
-የፊርማ ሂሳብ ለአሰልጣኝ እስከ 200ሺ ለተጨዋች እስከ 00ሺ ብር እየታሰበ ነው
-ፌደሬሽኑ የዳታ ቤዝ ማሽን ይገጥማል
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀጣይ የውድድር ዘመን በተጨዋቾች ዝውውር ገበያ በደሞዝ ክፍያ፤ በክለቦች አደረጃጀትና በፌደሬሽን አንዳንድ አሰራሮች ከፍተኛ ለውጦች እየታዩ መሆናቸው ተስተዋለ፡፡ የ
በኦል አፍሪካን ጌምስ ለኢትዮጵያ 12 ሜዳልያዎች ሲገኙ 15 ስፖርተኞች ጠፉ
በሞዛምቢክ ዋና ከተማ ማፑቶ እየተካሄደ የቆየው 10ኛው ኦል አፍሪካ ጌምስ ነገ የሚገባደድ ሲሆን በአትሌቲክስ ውድደሮች የኬንያውያን የበላይነትን ኢትዮጵያውያን በመቀናቀን ከዳጉ የዓለም ሻምፒዮና የላቀ ስኬት አስመዘገቡ፡፡ እስከ ሐሙስ በተደረጉ ውድድሮች የኢትዮጵያ አትሌቶች 4 የወርቅ፤ 5 ብርና 3 የነሐስ ሜዳልያዎች አግኝተዋል፡፡ በተለይ በ10ሺ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች የወርቅ ሜዳልያዎችን ኢብራሂም ጄይላንና ሱሌ ኡታራ ሲያገኙ በሴቶች 5ሺ ሜትር የመከላከያዋ አትሌት ሱሌ ኡታራ 2ኛ የወርቅ ሜዳልዋን በመውሰድ በድርብ ድል ደምቃለች፡፡
የየሊጎቹ ሻምፒዮኖች ተተነበ
በአውሮፓ 5 ታላላቅ ሊጎች የውድድር ዘመኑ ከተጀመረ 1 ወር ሲሞላው ሲአይኢኤስÂ ራኒንግ ቦል የተባሉ ሁለት ተቋማት በትብብር ባካሄዱት ጥናት በእንግሊዝ ቼልሲ፤ በስፔን ባርሴሎና፤ በጀርመን ባየር ሙኒክ እንዲሁም በፈረንሳይ ፓሪስ ሴንትዠርመን የሻምፒዮናነት እድል እንዳላቸው ገመቱ፡፡ በተቋማቱ የሚገኙ ተመራማሪዎች ይህን በጥናት ላይ የተመሰረተ ትንበያቸው ለማዘጋጀት በዋናነት ሶስት መስፈርቶችን ተከትለዋል፡፡ የክለቦችና የተጨዋቾች ልምምድና የዝግጅት ብቃት፤ የዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሞክሮና የቡድኖች የተረጋጋ ስብስብ ዋና መለኪያቸው ነበሩ፡፡
የፍልስጤሞች ነፃ መንግሥት ይሳካ ይሆን?
ከአውሮፓ አገራት ድጋፍ እያገኙ ነው
ጥላሁን አክሊሉ
በሚቀጥለው ሳምንት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብና የተለያዩ ሚዲያዎችን ትኩረት የሚስብ ስብሰባ በኒውዮርክ
የተባበሩት መንግሥታት /ቤት ውስጥ ይካሄዳል፡፡ የስብሰባው ዓላማም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፣ ያለ
መንግሥት የኖረችውን የፍልስጤም ነፃ መንግስት ለመመስረት የሚካሄድ ስብሰባ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት 192 ሲሆኑ፣ ፍልስጤማዊያን የራሳቸውን መንግስት ለመመስረት የ128 አባል አገሮች ወይም 2/3ኛ ድም ማግኘት አለባቸው፡፡
ኮከብ ይወለዳል፤ ይከሰታል፤ ይፈጠራል ኢትዮጵያዊቷ ሃና እና አሜሪካዊቷ ጃኪ
ጃኪ ኢቫንቾ
ጃኪ ኢቫንቾ የ11 አመት አሜሪካዊ ነች - በአስደናቂ የድምፅ ችሎታ አሜሪካዊያንን ያማለለች፡፡ አምና በ..ጎት ታለንት.. ውድድር ላይ ስትዘፍን፤ በድምጿ የተማረኩ አሜሪካዊያን ልብ ውስጥ ገባች፡፡ ጃኪ ኢቫንቾ፤ በጣም ተወዳጅ የሆነችው በተራ ዘፈን አይደለም - በጣም ከባድ እንደሆነ በሚነገርለት የኦፔራ አዘፋፈን እንጂ፡፡ ምን ልታስቡ እንደምትችሉ ይገባኛል፡፡ ከኢትዮጵያን አይዶል ተወዳዳሪዋ ከሃና ግርማ ጋር ተመሳሳይነታቸው ይገርማል - በእድሜያቸው፣ በኦፔራ አዘፋፈናቸው፣ በአስደናቂ የድምፅ አቅማቸው፣ ከውድድር ባገኙት ተወዳጅነት...፡፡ አጀማመራቸውስ?
..የቅጂ መብት ጥሰት መንግስትን የመገልበጥ ያክል ነው..
በ1955 ዓ.ም በአሜሪካ ኢሊኖይስ ግዛት የተወለደው ቢል ላስዌል የታወቀ ሙዚቃ አቀናባሪ እና ፕሮዱዩሰር ነው፡፡ ለ25 ዓመታት በሙዚቃ ሙያ የዘለቀው አሜሪካዊው አርቲስት፤ ከ700 በላይ አልበሞች ፕሮዲዩስ አድርጓል፡፡ በሙዚቃ ዙሪያ በርካታ ጥናትና ምርምር በማድረግና አዳዲስ አቀራረቦችን በመፍጠር በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ግንባር ቀደም ባለሞያ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ የሬጌን ሙዚቃና የቦብ ማርሌን ሥራዎች ለዓለም በማስተዋወቅ ከሚታወቀው ክሪስ ብላክ ዌል ጋር በመስራት የራሱን አስተዋኦ ያበረከተ አርቲስት ነው፡፡ ይሄ ባለሙያ የታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት ድምፃዊ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ባለቤት ነው፡፡ ቢል ላስዌል በጂጂ ተወዳጅ ሙዚቃዎች ውስጥ በአቀናባሪነትና በፕሮዲዩሰርነት አሻራውን አሳርፏል፡፡ ጳጉሜ 6 ቀን 2003 ዓ.ም ኢትዮጵያን ከመልቀቁ ከሁለት ሰዓት በፊት ካረፈበት የኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ውስጥ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው በሙያውና በህይወቱ ዙሪያ አነጋግራዋለች፡፡
አንዱን ለመካብ ሌላውን ማንኳሰስ!
ሐምሌ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. እዚሁ ጋዜጣ ላይ ..ፖለቲካና የደራሲ ፖለቲከኞች.. በሚል ርዕስ በደራሲ
አለማየሁ ገላጋይ የተጻፈውን ጽሁፍ ””ደራሲW ዋና መሽከርከሪያ ርዕሰ ጉዳያቸው አድርገው የተነሱበት ..የኢትዮጵያ የተገለባባጭ ደራሲ ደሀ አይደለችም... ከጥቂቶቹ ደራሲያን በስተቀር አብዛኞቹ ደራሲያን ጉልበታም የፖለቲካ ወጀብ የሚያስጎነብሳቸው መንፈሰ ድውያን ናቸው.. የሚለው ነው፡፡በተያያዘ ነጥባቸውም ..ፎርመኛ ደራሲዎች አሉን.. ያሏቸውን እነ ብርሀኑ ዘሪሁን፣ ፀጋዬ ገ/መድህንና ሌሎችንም አንስተው ባልተገባ የሀሳብ አካሄድ ወይም ውቅያኖስን በጭልፋ... በሚመስል ቁንጽል ዕይታ ሀሳባቸውን ሲያስነብቡን በዝምታ አለፍን፡፡ እሳቸው ግን ዝምታችንን ..አበጀህ.. እንደመባል ቆጥረውት ቀጥለውበታል፡፡
..አይቻልም ወይ መኖር ሥልጣን ላይ ሳይወጡ.. ፓርቲ ያረጃል እንዴ?
የዛሬ ወጋችን ከፖለቲካና ከስልጣን ጋር የተገናኘ ነው - ለነገሩ ዓምዱም ፖለቲካ በፈገግታ ይል የለ! ስለ ፖለቲካ ማውራታችን ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ ፖለቲካን ማውራት እንጂ መተግበር አልወጣኝም፡፡ ለጊዜው እኛ አገር ፖለቲካ ሲወራ እንጂ ብዙም ደስ አይልም፡፡ ስለዚህ ፖለቲካ በፈገግታችን ይቀጥላል፡፡ ለከወደ አሜሪካ በተገኘ ቁም ነገር ያዘለ ቀልድ እንጀምረው - ወጋችንን፡፡
የዘመን ሐሳበ
የኢትዮጵያ ዘመን መቁጠሪያ መሠረቶች
ዘመን ማለት በመላው ጊዜ ውስጥ የሚገኝ፤ በልብ ውስጥ የሚያዝ ወሰነ ጊዜ፣ ቀጠሮ ጊዜ፣ ጊዜ ዕድሜ ነው፡፡ ዘመን ማለት ቁጥር ያለው ጊዜ ነው፡፡ ጊዜ የተባለው ምንት ዓለም ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ እስካለችበት ጊዜ ድረስ የሚኖር ያለ ሲሆን ይህን ጊዜ ከፍሎ ወሰን፣ ድንበር፣ ቀጠሮን አድርጐ በጊዜ ውስጥ ያሉ ጊዜያትን ቁጥር እሚያደርግለት ደግሞ ዘመን ነው ብሎ፣ በምኑም ምኑም ፈጽሞ መሳይ የሌለው የኢትዮጵያ ሐሳበ ዘመን ተረድቶ - አስረድቶ፤ ጊዜውን በዘመን የመለየትና የማስለየት ሥራውን ይጀምራል፡፡